Saturday, 25 December 2021 13:13

ከታላላቆች አንደበት

Written by 
Rate this item
(0 votes)

• ህይወት ብስክሌት እንደ መጋለብ ነው። ሚዛንህን ለመጠበቅ መጓዝህን መቀጠል አለብህ።
• ሦስት ትላልቅ ኃይሎች ዓለምን ይገዟታል፡- ድድብና፣ ፍርሃትና ስግብግብነት።
• ተማሪ የምትሞላው ከረጢት አይደለም፤ የምትለኩሰው ችቦ እንጂ፡፡
    (አልበርት አንስታይን)
***
• እውነታ የሚፈጠረው በአዕምሮ ነው፤ የምናስበውን በመለወጥ እውነታችንን መለወጥ እንችላለን።
• ሰው ቀድሞ ራሱን ሳያሻሽል ዓለምን ማሻሻል አይችልም፡፡
• ራስን ማሸነፍ የድሎች ሁሉ ድል ነው።
   (ፕሌቶ)
***
• እንባ የሚመነጨው ከልብ እንጂ ከአዕምሮ አይደለም።
• እውነት የጊዜ ብቸኛዋ ሴት ልጅ ነበረች።
• መማር ፈጽሞ አዕምሮን አያደክምም።
• ተፈጥሮ የራሷን ህጎች ፈጽሞ አታፈርስም፡፡
   (ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ)


Read 1117 times