Print this page
Saturday, 25 December 2021 13:23

የህንዳውያን አባባሎች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

• ፈጣሪ ነብርን በመፍጠሩ አትውቀሰው፤ ይልቁንም ክንፍ ስላልሰጠው አመስግነው።
•እኛ ወደ ፈጣሪ አንድ እርምጃ ስንጠጋ፣ እሱ ወደኛ ሰባት እርምጃ ይጠጋል።
• ህይወት ድልድይ ነው፤ ተሻገርበት፤ ነገር ግን ቤት እንዳትገነባበት።
• በዓይነስውሮች መካከል ባለ አንድ ዓይን ንጉሥ ነው።
• የልብ ወዳጅ ያለው ሰው መስተዋት አያስፈልገውም።
• ምግብህን በሌላ ሰው ገበታ ላይ ተቀምጠህ አትብላ።
• ብልጥ ወንድ ፈፅሞ ብልጥ ሴትን አያገባም።
• እያንዳንዱ ውሻ በሰፈሩ ነብር ነው።
• መበደር ችግር መሸመት ነው።
• መርፌ በገባበት ክር ይከተላል።
• ልብ ያልፈለገውን ዓይን አያየውም።
• መድኃኒትም ተጠቀም፤ ፀሎትም አድርስ።
• እንደ ባሪያ የሚሰራ እንደ ንጉሥ ይበላል።
• ምሬት (ስሞታ) የደካሞች መሳሪያ ነው።
• ያለ ፍቅር ሁሉም  ከንቱ ነው።

Read 1102 times
Administrator

Latest from Administrator