Saturday, 25 December 2021 13:24

የነገር ጥግ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 በ1980ዎቹ ግድም ነው፡፡ አንዲት ብልህና ብሩህ ኢትዮጵያዊት የውጭ የትምህርት ዕድል ታገኝና ወደ አማሪካ ትሻገራለች፡፡ ብዙም ሳትቆይ ኮሌጅ ትገባለች፡፡ ትምህርቷን ትቀጥላለች። ጓደኞችም ታፈራለች፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከኮሌጅ ጓደኞቿ ጋር ሻይ ቡና እያሉ ይጨዋወታሉ፡፡ አሜሪካውያን ጓደኞቿ ከድሃና ኋላቀር አገር መምጣቷን ያውቃሉ።
እናም በጨዋታቸው መሃል አንደኛዋ አሜሪካዊት፤ “አገራችሁ ግን የት ነው የምትኖሩት? ቤት አላችሁ?” ስትል ትጠይቃለች፡፡
ኢትዮጵያዊቷም፡- “ዛፍ ላይ ነው የምንኖረው” አለቻት፤ ፍርጥም ብላ፡፡
ፈረንጂቱም በፈገግታ ወደ ጓደኞቿ እያየች፤ “ይኸው…. አላልኳችሁም!” ትላቸዋለች፤ በድል አድራጊነት፡፡
 ሌላዋ ደግሞ “ታዲያ ወደ መኝታ ቤታችሁ በምንድን ነው የምትሔዱት?” ስትል ትጠይቃለች፡፡
የኛይቱ ጀግኒትም ፈጠን ብላ፤ “በሊፍት!?” አለቻት፡፡
(ዛፍ ላይ እንኳን ሊፍት ሰርተናል ማለቷ ነው!)


Read 1024 times