Saturday, 25 December 2021 13:36

አቡነ ዜና ማርቆስ ያሰለጠናቸውን 83 ሴቶች አስመረቀ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     አቡነ ዜና ማርቆስ የህፃናትና አረጋውያን መርጃ በህይወት ክህሎትና በንግድ ስራ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 83 ሴቶች ባለፈው ቅዳሜ በላፍቶ ሞል አስመረቀ።  በ2002 ዓ.ም በአንዲት ሴት የተመሰረተውና ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ችግሮች ወድቀው ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ የነበሩ ሴቶችን ልጆቻቸውንና አረጋውያንን ከየወደቁበት እያነሳ አስፈላጊውን እንክብካቤና ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱም ታውቋል። ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ 701 ህፃናትን 335 እናቶችንና አረጋውያንን ሲደግፍ ቆየው  አቡነ ዜና ማርቆስ የህጻናትና የአረጋውያን መርጃ ማዕከል በተለይ እናቶችን ለ10 ቀናት የስራ ክህሎት ስልጠናና የስራ መነሻ ገንዘብ በመስጠት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲንከባከቡና የቁጠባ ባህል እንዲለምዱ በማድረግ ከፍተኛ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ሃላፊዎቹ ተናራዋል። በእለቱም በመርጃ ድርጅቱ ተደግፈው ለስኬት የበቁ ሴቶች  ተሞክሯቸውን ያካፈለ ሲሆን  የሙዚቃና የመዝናኛ መሰናዶም ቀርቧል።

Read 12916 times