Saturday, 25 December 2021 13:37

“አዲስ ህይወት” እና “ከማዕዘኑ ወዲህ” መፅሐፎች ዛሬ ይመረቃሉ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     የሕግ ባለሙያና ደራሲ ዳግማዊ አሰፋ ያዘጋጃቸው “አዲስ ህይወት” እና “ከማዕዘኑ ወዲህ የተሰኙ ሁለት መጽሐፍት ዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ይመረቃል። ወጣቱ የህግ ባለሙያ ዳግማዊ አሰፋ በሀዋሳ ከተማ ከጓደኛው የሕግ ባለሙያ ዳንኤል ጋር የጥብቅና ስራዎችን እየሰራ ባለበት ቢሯቸው ድረስ መጥቶ ጥይት በከተኮሰባቸው አንድ ግለሰብ ጓደኛው ዳንኤል ህይወቱ ሲያልፍ ዳግማዊ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶበት ተዓምር  በሚመስል ሁኔታ የተረፈ ሲሆን ይህ ወጣት ከአንገቱ በታች ያለ  ሰውነቱ በሙሉ አይታዘዝም።
ይሁን እንጂ ሰዎች ከእሱ ጥንካሬ ይማሩ ዘንድ በአደጋው የደረሰውን ጉዳት፣ የህክምና ሂደት፣ ከሞት የተረፈባቸውን ከባድ ሂደቶች፣ ስለይቅርታና ምህረት፣ ስለመንፈስ ጥንካሬውና አሁን ተቀብሎት ስለሚኖረው ዊልቸር ላይ ስላለው ህይወቱ የሚገልጽ እጅግ አሳዛኝና አስተማሪ መፅሐፎቹን ለንባብ አብቅቷል። እነዚህ መፅሐፍት ዛሬ በብሔራዊ ቴአትር ሲመረቁ ደራሲውን ጨምሮ ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ፣ አርቲስት ስዩም ተፈራ፣ ወግ አዋቂው በሃይሉ ገ/መድህን፣ አንዷለም አባተ (ዶ/ር) (የአፀደ ልጅ)፣ አቶ ዘመዱ ደምስስና ገጣሚያኑ ህሊና ደሳለኝ፣ በለው ገበየሁና ባርያስ በዛብህ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
“አዲስ ሕይወት” እና “ከማዕዘኑ ወዲህ” መፅሐፍትም በዋናነት በጃዕፋር መፅሐፍት መደብር እየተከፋፈሉ እንደሆነም ታውቋል።



Read 13627 times