Print this page
Saturday, 25 December 2021 13:42

“ዛሬም አለሁ” ግለ-ታሪክ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ደራሲ ትዕግስት ሙሉጌታ የራሷን ታሪክ ያሰፈረችበት “ዛሬም አለሁ” ግለ-ታሪክ መጽሐፍ ዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ በላፍቶ ሞል አርት ጋለሪ ይመረቃል።
ባለታሪኳ ፀሐፊ ትዕግስት ሙሉጌታ እጅግ የሚገርሙ የሚያስደነግጡና ሌሎቻችን ለመግለጽ የማንደፍራቸውን አስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረዶች ሌላው ይማርበት ዘንድ መጻፏን ተናግራለች። በመፅሐፉ ሴት ሆኖ ጥቃትንና የአካል ጉዳትን ተከትሎ የሚመጣን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስነልቦናዊ ጫናዎችን ተቋቁሞ የማለፍን ትዕግስትና ጥንካሬ የያዘ ነውም ተብሏል። በ191 ገጽ በተቀነበበው “ዛሬም አለሁ” የመፅሐፍ ምረቃ ላይ በርካታ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች፣ የመፅሐፍ ዳሳሰና ንግግሮች የሚቀርቡ ሲሆን፣ በዕለቱም ጋዜጠኞች፣ በሴቶች ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ተወካዮችና የፀሐፊዋ ጓደኞች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።

Read 13253 times