Sunday, 26 December 2021 00:00

የቬንዙዌላ 2,700% የዋጋ ግሽበት በአመቱ ከአለም 1ኛ ሆኗል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 በተገባደደው የፈረንጆች አመት 2021 በሁሉም የአለማችን አገራት የዋጋ ግሽበት በተለያየ መጠን ጭማሬ ቢያሳይም የቬንዙዌላን ያክል ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስመዘገበ አገር እንደሌለ የተነገረ ሲሆን  የአገሪቱ አመታዊ የዋጋ ግሽበት 2,700% መድረሱን ፋይናንስ ማጋዚን ድረገጽ አስነብቧል፡፡
ቬንዙዌላ ላለፉት አራት ተከታታይ አመታት በዋጋ ግሽበት ከአለማችን አገራት በቀዳሚነት እንደዘለቀች ያስታወሰው ዘገባው፣ ከእነዚህ አመታት ከፍተኛው እ.ኤ.አ በ2018 የተመዘገበው የ65,374% የዋጋ ግሽበት መሆኑንም አክሎ ገልጧል፡፡
በድረገጹ መረጃ መሰረት በ2021 ሁለተኛውን ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስተናገደችዋ አገር ሱዳን ስትሆን፣ የዋጋ ግሽበቱ 194.6% መሆኑንም አክሎ ገልጧል።
ዚምባቡዌ በ92.5%፣ ሱሪኔም በ54.4%፣ የመን በ40.8% የዋጋ ግሽበት እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ የያዙ የአለማችን አገራት መሆናቸውም መረጃው ይጠቁማል።
በ2021 የፈረንጆች አመት እጅግ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የታየባት የአለማችን አገር ሳሞኣ ስትሆን የዋጋ ግሽበቱ –3.0% መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፣ ኮሞሮስ፣ ሴንት ኪትስ ኤንድ ኔቪስ፣ ማካኦ ሳርና ጃፓን እንደሚከተሉም አክሎ ገልጧል፡፡

Read 2793 times