በተገባደደው የፈረንጆች አመት 2021 በሁሉም የአለማችን አገራት የዋጋ ግሽበት በተለያየ መጠን ጭማሬ ቢያሳይም የቬንዙዌላን ያክል ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስመዘገበ አገር እንደሌለ የተነገረ ሲሆን የአገሪቱ አመታዊ የዋጋ ግሽበት 2,700% መድረሱን ፋይናንስ ማጋዚን ድረገጽ አስነብቧል፡፡
ቬንዙዌላ ላለፉት አራት ተከታታይ አመታት በዋጋ ግሽበት ከአለማችን አገራት በቀዳሚነት እንደዘለቀች ያስታወሰው ዘገባው፣ ከእነዚህ አመታት ከፍተኛው እ.ኤ.አ በ2018 የተመዘገበው የ65,374% የዋጋ ግሽበት መሆኑንም አክሎ ገልጧል፡፡
በድረገጹ መረጃ መሰረት በ2021 ሁለተኛውን ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስተናገደችዋ አገር ሱዳን ስትሆን፣ የዋጋ ግሽበቱ 194.6% መሆኑንም አክሎ ገልጧል።
ዚምባቡዌ በ92.5%፣ ሱሪኔም በ54.4%፣ የመን በ40.8% የዋጋ ግሽበት እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ የያዙ የአለማችን አገራት መሆናቸውም መረጃው ይጠቁማል።
በ2021 የፈረንጆች አመት እጅግ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የታየባት የአለማችን አገር ሳሞኣ ስትሆን የዋጋ ግሽበቱ –3.0% መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፣ ኮሞሮስ፣ ሴንት ኪትስ ኤንድ ኔቪስ፣ ማካኦ ሳርና ጃፓን እንደሚከተሉም አክሎ ገልጧል፡፡