Print this page
Monday, 27 December 2021 00:00

ዴንማርክ ለ300 እስረኞች ከኮሶቮ በ210 ሚ. ዩሮ እስር ቤት ልትከራይ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)


              በተለያዩ ወንጀሎች በቁጥጥር ስር የምታውላቸው እስረኞች ብዛት ያማረራት ዴንማርክ 300 እስረኞችን የምታቆይበትን እስር ቤት በ210 ሚሊዮን ዩሮ ከኮሶቮ ልትከራይ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ዴንማርክ ተጨማሪ 1000 እስር ቤቶች እንደሚያስፈልጋትና 300 ያህሉን በጊዜያዊነት ወደ ኮሶቮ ለመላክ ማቀዷን የዘገበው ዘ ጋርዲያን፣ የኮሶቮ የፍትህ ሚኒስትርም እስረኞችን ለ10 አመታት በኪራይ እስር ቤት ለማቆየት መፍቀዱንና ስምምነቱ በመጪው ሰኞ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ማረጋገጣቸውን አመልክቷል፡፡
እስረኞቹ የተፈረደባቸውን የእስር ጊዜ ሲያጠናቅቁ ወደ ዴንማርክ እንደሚመለሱ የተነገረ ሲሆን፣ ኮሶቮ ከ1 ሺህ 600 በላይ የራሷ እስረኞች እንዳሏት የጠቆመው ዘገባው፣ ከዚህ ቀደም ኖርዌይና ቤልጂየም ከሆላንድ እስር ቤት ተከራይተው እንደነበርም አስታውሷል፡፡



Read 1188 times
Administrator

Latest from Administrator