Print this page
Monday, 27 December 2021 00:00

ቲክቶክ በ2021 በብዛት የተጎበኘ ድረገጽ ተባለ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

   በአለማቀፍ ደረጃ ተወዳጅነትን ያገኘው ቲክቶክ የተባለው የአጫጭር ቪዲዮዎች ማጋሪያ አፕሊኬሽን በፈረንጆች አመት 2021 በብዛት የተጎበኘ የአለማችን ቀዳሚው ድረገጽ በመባል ከጎግል ክብሩን መቀበሉ ተነግሯል፡፡
ክላውድፍሌር የተባለ ተቋም ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፣ ባለቤትነቱ የቻይናው ኩባንያ ባይትዳንስ የሆነው ቲክ ቶክ ካለፈው አመት የካቲት ወር ጀምሮ በጎብኝዎች ብዛት ቀዳሚነቱን በመያዝ በ1ኛነት አመቱን ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
ባለፈው አመት በኢንተርኔት በብዛት በመጎብኘት የ7ኛ ደረጃ ላይ የነበረው ቲክ ቶክ ዘንድሮ ግን የአምናውን መሪ ጎግል ወደ ሁለተኛነት ዝቅ በማድረግ ቀዳሚነቱን መያዙን የጠቆመው ዘገባው፣ ቲክ ቶክ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ተጠቃሚዎችን ለማፍራት መቻሉንም አመልክቷል፡፡

Read 2832 times
Administrator

Latest from Administrator