Print this page
Saturday, 01 January 2022 00:00

ወመዘክርና ለባዊ አካዳሚ የተከፈቱት ቤተመጽሐፍት ተመረቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ እና ለባዊ አካዳሚ በጋራ የከፈቱት የሕዝብ ቤተመጻህፍት ቅዳሜ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ተመርቆ ስራ ሊጀምር ነው። ቤተ መጽሀፍቱ “ወመዘክር  በለባዊ” የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን የራስ ካሳ ሃይሉ የልጅ ልጅ የሆኑት የደጃዝማች አምሃ አበራ ካሳ ስብስብ መፅሀፍትንና ወመዘክር የገዛቸውን በርካታ ተለያዩ መጽሀፍት የያዘ መሆኑም ታውቋል። በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የወመዘክር ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ገጣሚና ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲና መምህር ሀይለመለከት መዋዕል፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የስነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ አዳነ ድልነሳው እንዲሁም የለባዊ አካዳሚ የ12ኛ ክፍል ተማሪዋ ላዕማሮት ማሞ ስለ ቤተመጻህፍት ፋይዳ የየራሳቸውን ምልከታ አቅርበዋል። በአንድ ጊዜ እስከ 50 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችለው ቤተ-መጽሐፍቱ በቅርቡ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናልም ተብሏል።

Read 13752 times
Administrator

Latest from Administrator