Sunday, 02 January 2022 20:39

አሸዋ ቴክኖሎጂ አርቲስት ናርዶስ አዳነን ብራንድ አምባሳደር አድጎ ሾመ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በአጭር ጊዜ ውስጥ እውቅና ያተረፈውና በኢኮሜርስ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማራው አሸዋ ቴክኖሎጂ እውቋን ተዋናይት ናርዶስ አዳነን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።  ኩባንያው ለህልውና ዘመቻውና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚ. ብር ለመሰብሰብ አቅዷል። አሸዋ ቴክኖሎጂ በወጣት ባለራዕዮች የተመሰረተና ዘመኑ የፈጠራቸውን ቴክሎጂዎች በመጠቀም ግብይትንና ሸማቾችን ለማዘመን እየሰራ ስመሆኑ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል። አቶ ዳንኤል ይህን የገለፁጽ ባለፈው ሳምንት  በጌት ፋም ሆቴል አርቲስት ናርዶስ አዳነን በብራንድ አምባሳደርነት ባስፈረሙበትና “ገናን ከወገኔ ጋር” የተሰኘ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብርን ይፋ ባደረጉበት ጊዜ ነው። አርቲስት ናርዶስ የአሸዋ ቴክሎጂ ብራንድ አምባሳደር ሆና ከመስራቷም ባለፈ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩንም ታስተባብራለች-ተብሏል።
አሸዋ ቴክኖሎጂ ከድርጅቱና ከሰራተኞቹ በማሰባሰብ 500 ሺህ ብር ለተፈናቃዮች ለመለገስ ያሰበ ሲሆን ቀሪውን ከዲስፖራው፣ ከንግዱ ማህበረሰብና ከበጎ ፈቃደኞች ለማሰባሰብ ማሰቡን አቶ ዳንኤል ገልጸዋል። የኩባንያው 50 ሰራተኞችም ደም ይለግሳሉ ተብሏል።

Read 19644 times