Sunday, 09 January 2022 00:00

ክብር ለመከላከያ - የቦክስና የሰርከስ ትርኢቶች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ክብር ለመከላከያ ሰራዊታችን የተሰኘው ኢምር በኮልፌ 2014 ቶርናመንት  ጥር 1/2014 በኮልፌ መላጣ ሜዳ በከፍተኛ ድምቀት ተካሄደ።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ጀግኖች ተመስግነዋል፣ ለሀገራቸው ከፊት የቀደሙ ተወድሰውበታል፣ ኢትዮጵያን ዘብ በመሆን ሁሌም የሚያገለግሉ ተዘክረዋል። እንዲሁም የደም ልገሳ እና በስፖርት ጋዜጠኞች እና በኮሜዲያን መካከል የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሂዷል፣ የቦክስ እና የሰርከስ ትርኢቶች የፕሮግራሙ ድምቀቶች ነበሩ።
ፕሮግራሙ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚዎች፣ አርቲስቶች፣ የቀድሞ የእግር ኳስ ዝነኛ ተጨዋቾች እንዲሁም የኮልፌ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።



Read 7030 times