Print this page
Sunday, 09 January 2022 00:00

Diabetes (የስኩዋር ሕመም) ልጅ ላለመውለድ….

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ
Rate this item
(1 Vote)

ምክር እፈልጋለሁ የሚል መነሻ ያለው አስተያየት ያገኘነው ከአንዲት የሰላሳ ሰባት አመት እድሜ ካላት ሴት ነው፡፡ መልእክትዋ እንደሚከተለው ነው፡፡
‹‹…ትዳር ከመሰረትኩ አሁን ስድስተኛ አመቴ ነው፡፡ ባለቤቴ በእድሜ ከእኔ በአስራ ሁለት አመት ከፍ ይላል፡፡ ተዋውቀን…በደስታ ተፋቅረንና ተከባብረን የመሰረትነውን ትዳር በአግ ባቡ እየመራን ነው፡፡ ግን አንድ ነገር ተቸገርን፡፡ እሱም ልጅ መውለድ አለመቻሌ ነው፡፡ ሁኔ ታውን አንዳ ንድ ጊዜ አንስተን ስንወያይ የእሱ አስተያየት …እኔ መውለድ ሳልችል ቀርቼ እንጂ ከእሱ በኩል ምንም ችግር እንደሌለው ነው የሚነግረኝ፡፡ ግራ ሲገባኝ ነገሩን ለጉዋደ ኞቼ ማማከር ጀመርኩ። ሁለታችሁም ወደሐኪም ሄዳችሁ ተመርመሩ የሚል ምክር አገ ኘሁ፡፡ ይህንን ስነግረው ሊስማማ አልቻለም፡፡ ብትፈልጊ አንቺ ሂጂና ታከሚ እንጂ እኔ አልሄድም የሚል ነበር መልሱ፡፡ ቢቸግረኝ ለወንድምየው አማከርኩት፡፡ እሱም ወደሆስፒ ታል መሄድ እንዳለብንና ሕክምና ማግኘት ጠቃሚ መሆኑን አስረድቶ አሳመነው፡፡ የሐኪም ቀጠሮ ይዣለሁ እና እንሂድ ስለው…አ..አ..ይ…አንቺ ሂጂ…እኔ ከስራ ስወጣ እሄዳለሁ አለኝ፡፡ እሺ ብዬ ሄጄ ታየሁ፡፡ ምንም ችግር እንደሌለብኝና ባለቤቴን ይዤ መቅረብ እንደሚ ገባኝ ተነገረኝ፡፡ በሀሳቡ ብስማ ማም ያው ነግሬዋለሁ በሚል ዝም አልኩ። እሱ ግን አልሄ ደም፡፡ በሁዋላም ጭምጭ ምታ ወሬ ሰማሁ። ጉዋደኛው እንደነገረኝ….ከአሁን ቀደምም ያገባትን ልጅ የፈታው በህመሙ ምክንያት ልጅ መውለድ አትችልም የሚል መልስ ከሐ ኪም በማግኘቱ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ የስኩዋር ታማሚ ስለሆነ ልጅ የመውለድ አቅሙን ያዳከመው መሆኑን እና የተቻለውን ያህል ሕክምናው እንደሚደረግለት ተነግሮት እንደነበር አስታውሳለሁ አለኝ፡፡ ለሐኪሜም ሳማክረው …ሊሆን ይችላል …ግን ይምጣና ይታይ…. አለኝ፡፡
የእኔ ጥያቄ የስኩዋር ሕም,መም ከወላጅ ወደ ልጅ ከመተላለፉ በስተቀር ልጅ ላለመውለድ ምክንት ሊሆን ይችላልን ?...››
ይህ ጥያቄ የብዙዎች ስለሚሆን ከተለያዩ መረጃዎች ምላሽ የሚሆን ነገር አፈላልገን ወደአማርኛ በመመለስ ለንባብ ብለናል፡፡
የስኩዋር ሕመም በወንዶችም ይሁን በሴቶች ላይ ልጅ ላለመውለድ ምክንያት ሊሆን ይች ላል፡፡ የዚህም ምክንያቱ የስኩዋር ሕመም ያለበት ወንድ Sperm…የዘር ፈሰሹን አቅም እና ጥራት ሊያዳ ክምበት ስለሚችልና እንዲሁም በሴትዋ በኩል ለእርግዝና ዝግጁ የሆነ ወይንም ጥራቱ የተሟላ እንቁላል እንዳይኖር ምክንያት ስለሚሆን ነው፡፡
Yashoda Hospitals | Sep 14, 2018  የተባለው ድረገጽ እንደሚገልጸው የስኩዋር ሕመም ልጅ ለመውለድ የሚያስችለውን ሂደት የሚመራውን ሆርሞን ተግባሩ እንዲዘገይ ወይንም እንዳይሳካ ሊያደርግ ስለሚችል ልጅ ለመውለድ አቅም ሊያሳጣ ይችላል፡፡ የስኩዋር ሕመም በአይነት በሁለት የሚከፈል ሲሆን ቁጥር አንድ የስኩዋር ሕመም የሚከሰተው ከሰው ነት የውስጥ አካል አንዱ የሆነው ጣፊያ በቂ ኢንሱሊን የማያመርት ከሆነ ነው፡፡ በሰውነት ውስጥ የሚመረተው ኢንሱሊን ከነጭርሱ የማይመረት ከሆነ ወይንም የተመረተው ኢን ሱሊን ምንም የማይሰራ ከሆነ ቁጥር ሁለት ዲያቤቲክስ ወይንም የስኩዋር ሕመም ይከሰ ታል ማለት ነው፡፡ የአለም የጤና ድርጅት እንደሚገምተው በአለም ላይ ከ 180 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የስኩዋር ሕመም ያለባቸው ሲሆን ቁጥር አንድ የስኩዋር አይነት በየአመቱ በ3% እየጨመረ የሚሄድ ሕመም ነው፡፡
የስኩዋር ሕመም ልጅ መውለድን በምን መንገድ ያውካል በሚል መረጃው ካሰፈረው ቁም ነገር የሚከተሉትን ወስደናል፡፡
የስኩዋር ሕመም የሴቶችን የዘር ማፍራት እድል እንዴት ይቀንሰዋል?
የስኩዋር ሕመም ያለባቸው ሴቶች ለአንዳንድ infection (መመረዝ) ይጋለጣሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ በተጨማሪም የመራቢያ አካላትን በተለይም የዘር መተላለፊያ ቱቦን ከጥቅም ውጭ ሊያደርግ እንደሚችል ይገመታል፡፡
የስኩዋር ሕመም ያለባቸው ሴቶች በሚያረግዙበት ወቅት በደማቸው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የግሉኮስ መጠን ስለሚኖር ጽንሱን እንዲቋረጥ ሊያደርገው ይችላል፡፡
የስኩዋር ሕመም ድካም ፤ድብርት፤ጭንቀት የመሳሰሉትን ስለሚያስከትል የወሲብ ግንኙነት ለማድረግ ፍላጎትን ሊቀንስ ይችላል። የሴት ብልት እርጥበትን ስለሚቀንስ ሴቶች በግንኙነት ጊዜ ደስታን ማጣትና የህመም ስሜት ሊኖራቸው ይችላል፡፡
የስኩዋር ሕመም ሴቶች ልጅ እንዳያረግዙ ወይንም እንዳይወልዱ በማድረጉ ረገድ የተወሰኑ ምክንያቶችን አንብባችሁዋል፡፡ አሁን ደግሞ የስኩዋር ሕመም ወንዶች ልጅ ለማስረገዝ እንዳይችሉ ከሚያደርጉዋቸው ምክንያቶች በመጠኑ ታነቡ ዘንድ እነሆ ብለናል፡፡
የስኩዋር ሕመም የወንዶችን የዘር ማፍራት እድል እንዴት ይቀንሰዋል?
ወሲብ መፈጸም አለመቻል የመጀመሪያው የስኩዋር ታማሚ ወንድ ዘር የማፍራት ችግር ምክንያት ነው፡፡ የወንድ ብልት በተገቢው ሁኔታ ግንኙነት ለማድረግ ካልተነቃቃ ወይንም ጥንካሬ ከሌለው ግንኙነቱን ማድረግ ስለማይችል ዘርን ማፍራት የማይታሰብ ነው፡፡
የስኩዋር ሕመም ያለበት ወንድ አእምሮው የወሲብ ግንኙነት ለመፈጸም ዝግጁ መሆን ይሳነዋል፡፡ የሰውነት ድካም፤መዛል፤ፍላጎት ማጣት የመሳሰሉት ነገሮች የወንዶችን የወሲብ ፍላጎት ይፈታተነዋል፡፡
ወንዶች ቁጥር አንድ ወይንም ቁጥር ሁለት የሚባለው የስኩዋር ሕመም ካለባቸው የዘር ፈሳሽ Sperm አቅምና መጠን እንዲሁም ፍጥነትን የሚቀንስ ወይንም የሚያዳክም ስለሆነ ወንዶች ዘር ለማግኘት ላይታደሉ ይችላሉ፡፡
ሴቶችም ሆኑ ወንዶች የስኩዋር ሕመም ታማሚ ከሆኑ የተለያዩ የህክምና እርዳታዎች እን ደሚደረግላቸው የታወቀ ነው፡፡ የስኩዋር ሕመም ያለባቸው ሰዎች ኢንሱሊን የሚባለው በደም ውስጥ ያለውን ስኩዋር መጠን የሚቆጣጠረው ንጥረ ነገር በሰውነታቸው ውስጥ ስለማይኖር በህክምና ኢንሱሊን እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡ በሕክምናው ዘርፍ ከክብደት ወይ ንም ከአመጋገብ ጋር በተያያዘ የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በተለይም ልጅ ከመውለድ ጋር በተያያዘ ውጤታማ የሆነ እና ልጅ መውለድ እንዲችሉ  የሚያደርግ የህክምና ክትትል የሚ ደረግ ስለሆነ ታማሚዎች የህክምና ክትትላቸውን በትክክል እንደያደርጉ ይመከራሉ፡፡
ለስኩዋር ታማሚዎች የሚደረገው የህክምና እርዳታ ሴቶች እንቁላል እንዲያዘጋጁና እንዲ ለቁ፤ ወንዶች ደግሞ የወሲብ ግንኙነት ችግር እንዳይኖር የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደአስፈላጊነቱ የቀዶ ሕክምና እርዳታ ሊደረግ ይችላል፡፡     
ለስኩዋር ታማሚዎች ልጅ ማግኘት የሚረዳ ከፍ ያለ የህክምና አገልግሎት፡-
ለወንድ የስኩዋር ታማሚ የደከመውን አካልና ጥራት እና ፍጥነት እንዲሁም ብቃት የሌለ ውን የዘር ፈሳሽ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንዲተካ ማድረግ ወይንም የዘር ፈሳሽ  በክትባት መልክ ለሴትዋ እን ቁላል መስጠት አንዱ የህክምና ዘዴ ነው፡፡
የሴት የስኩዋር ታማሚ ልጅ የመውለድ እድልን በላቦራቶሪ (in vitro fertilization) እንዲሳካላት ማድረግ ይቻላል፡፡
የስኩዋር ታማሚዎች ልጅ ማርገዝ እና መውለድ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ለዚህ በአእምሮ በቂ ዝግጅት ማድረግ ይገባል፡፡ ተቀዳሚው ነገር ማቀድ እና እራስን ማሳመን እንዲሁም ይሆናል ብሎ መዘጋጀት ነው፡፡ ልጅ የመውለድን ሀሳብ ለማሳካት ችግር ሊሆኑ የሚችሉትን ነገሮች ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ መቀነስ ፤አመጋገብን ማስተካከል፤ አቅምን ያማከለ ስራ መስራት እና የህክምና ባለሙያዎችን መመሪያ መከተል አስፈላጊ ነው፡፡
ማንኛውም ሰው ወንድ ሆነ ሴት የስኩዋር ታማሚ ከሆኑ እና ልጅ ለመውለድ ውጤታማ መሆን ካቃታቸው የአእምሮ፤ የማህጸንና ጽንስ እና ዘር የማፍራት …ወዘተ ባለሙያዎችን በቅርብ ሆኖ ማማከር ይገባል፡፡
ማንኛውም ሰው የተስተካከለ ጤና እንዲኖረው አመጋገቡን ማስተካከል እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና የህክምና ባለሙያዎችን ምክር መተግበር ብሎም በቂ ክትትል ማድረግ ጠቃሚ ነው ይላል ምንጭ ያደረግነው መረጃ፡፡ 

Read 6874 times