Wednesday, 12 January 2022 00:00

ቢኤምደብሊው 2.2 ሚ. መኪኖችን በመሸጥ አዲስ ታሪክ ሰራ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ታዋቂው የጀርመን የመኪና አምራች ኩባንያ ቢኤምደብሊው ከቀናት በፊት በተሸኘው የፈረንጆች አመት 2021 ብቻ ከ2.2 ሚሊዮን በላይ መኪኖችን መሸጥ መቻሉንና ይህም ቁጥር በታሪኩ ከፍተኛው እንደሆነ ከሰሞኑ አስታውቋል፡፡
በአመቱ ከፍተኛ የሽያጭ ጭማሪ ማስመዝገቡን ባለፈው ማክሰኞ ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ ያስነበበው ሮይተርስ፣ በአዲሱ አመትም ከፍተኛ ሽያጭና ትርፍ ለማስመዝገብ ማቀዱን አመልክቷል፡፡
በሌላ ተያያዥ ዜና ደግሞ፣ የጃፓኑ የመኪና አምራች ኩባንያ ቶዮታ ሞተር ኮርፖሬሽን በአሜሪካ ገበያ ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል መሪነቱን ይዞ የዘለቀውን ጄኔራል ሞተርስ ኩባንያ በመብለጥ በሽያጭ የአንደኛ ደረጃን መያዙ ተነግሯል፡፡
ቶዮታ በ2021 የፈረንጆች አመት በአሜሪካ ገበያ 2.3 ሚሊዮን ያህል መኪኖችን ለመሸጥ መቻሉን ባለፈው ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን የዘገበው ሮይተርስ፣ ጄኔራል ሞተርስ በበኩሉ 2.21 ሚሊዮን መኪኖችን ብቻ መሸጡን አመልክቷል፡፡
ቶዮታ በአመቱ የአሜሪካ ሽያጩ በ10 በመቶ ሲጨምር ጄኔራል ሞተርስ በበኩሉ በ13 በመቶ መቀነሱን የጠቆመው ዘገባው፣ ጄኔራል ሞተርስ እ.ኤ.አ ከ1931 አንስቶ በአሜሪካ ገበያ ከፍተኛውን የሽያጭ ድርሻ ይዞ ለዘመናት መዝለቁን አስታውሷል፡፡

Read 1182 times