Saturday, 15 January 2022 20:38

መንግስት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በስነምግባር ጥሰት እንዲጠየቁ ክስ አቀረበ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሞራል፣ የህግና የሙያ ስነምግባር ጥሰት በመፈጸማቸው በህግ እንዲጠየቁ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዓለም ጤና ድርጅት የበላይ ጠባቂ ቦርድ የቅሬታ ማመልከቻ አስገብቷል። መንግስት የድርጅቱ የገለልተኝት መርህ በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የተነሳ ጥያቄ ውስጥ መግባቱንም አመልክቷል።
ኢትዮጵያ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ግዙፉን የዓለም ጤና ድርጅት በሃላፊነት እንዲመሩ ያጨቻቸው ቢሆንም ግለሰቡ፣ ይህንን ከፍተኛ ሃላፊነት ከወሰደ ግለሰብ የሚጠበቅ ሙያዊ ገለልተኝነት እንዳላሳዩ፣ መንግስት ለቦርዱ ባቀረበው ቅሬታ ጠቁሟል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ በአሸባሪነት የተፈረጀው የሕውሃት ቡድን አባል ከመሆናቸውም ሌላ ለቡድኑ ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለጸው የቅሬታ ማመልከቻ፤ የህውሃት ሽብርተኛ ቡድን ወታደራዊ ድሎችን ሲያስመዘግብ ደስታቸውን እንደሚገልጹና ሰብአዊ ቀውሶች ሲፈጠሩም ግልጽ የሆነ አድልዎ እንደሚፈጽሙ አመልክቷል። በአጠቃላይ የዶ/ር ቴዎድሮስ ተግባር የድርጅቱን የገለልተኝነት መርህ የሚጥስና መልካም ስሙን የሚያጎድፍ መሆኑን የጠቀሰው የመንግስት የቅሬታ ማመልከቻ፤ ዳይሬክተሩ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተሳሳተ መረጃ ሲያቀርቡ እንደነበር ጠቁሟል። ዳይሬክተሩ የተባበሩት መንግስታት ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ መንግስት በተቃራኒ እንዲቆሙ የቴክኒክና የፋይናንስ እገዛን ሲያደርጉ መቆየታቸውንም አጋልጧል።
በእነዚህ ተደጋጋሚ የሙያ ስነምግባር ጥሰቶች የዓለም ጤና ድርጅት የቦርድ አመራሮች ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የሚመረምር ኮሚሽን እንዲያቋቁምና እርምጃ እንዲወስድ  መንግስት ለቦርዱ ባቀረበው የክስ ማመልከቻ ጠይቋል።

Read 8262 times