Print this page
Saturday, 15 January 2022 21:40

“አዲሱ አድዋ” የዘፈን ግጥም ውድድር ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ጃዝ አምባ የሙዚቃ ት/ቤት ከፈንድቃ የባህል ማዕከልና ከጁብሊ ኢቨንትስ ጋር በመተባበር፣ “አዲሱ አድዋ” የተሰኘ የዘፈን ግጥም ውድድር ሊያካሂድ ነው። ውድድሩ ከ18-35 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች የሚሳተፉበትና በሰላም፣ በአንድነት፣ በፍቅርና በአብሮነት ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ከየትም ያልተኮረጀና አዲስ ፈጠራ መሆን እንዳለበት  አዘጋጆቹ  ገልፀዋል፡፡ የግጥም ስራው በታዋቂ የግጥምና የዜማ ደራሲዎችና አቀናባሪዎች ተመዝኖ ሚዛን የደፋው አሸናፊ ይሆናልም ተብሏል። አሸናፊው የሙዚቃ ግጥምም  በትልልቅ የሙዚቃ ሰዎች ዜማ ተሰርቶለትና ተቀናብሮ ትልቅ ሙዚቃ ሆኖ እንደሚመዘገብም  አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
የሙዚቃ ግጥም ጸሀፊው አሸናፊነቱ በአድዋ በዓል ዕለት የሚገለጽ ሲሆን፣ ሙዚቃው በዩቲዩብና በተለያዩ አውታሮች ተጭኖ የሚያስገኘው ገቢ በጦርነቱ ለወደሙት ት/ቤቶችና  ሌሎች መሰረተ ልማቶች መልሶ መገንቢያ ይውላልም ተብሏል። ውድድሩም የተዘጋጀበት ዋና አላማም ወጣቱ  የአሁኑን የ”NO More” እንቅስቃሴ ከጥንቱ አድዋ ጋር አገናኝቶ፣ የነጻነቱንና የአሸናፊነቱን ገድል በጥልቅ እንዲረዳና የአሸናፊነት ስነ-ልቦና እንዲላበስ ታስቦ መሆኑን የጃዝ አምባ፣ ፈንድቃና ጁብሊ ኢቨንትስ ሃላፊዎች ተናግረዋል።


Read 1048 times