Saturday, 15 January 2022 21:45

“መኖር አሜሪካ” መጽሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በዲያስፖራው ደራሲ  ዓለማየሁ ማሞ ከ15 ዓመት በፊት ተጽፎ ተወዳጅነትን ያተረፈው “መኖር አሜሪካ” መጽሐፍ፤ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ ተሻሽሎና በይዘት ዳብሮ በድጋሚ መታተሙን ደራሲ አለማየሁ ገልጸዋል። የብዙዎች ምኞትና ናፍቆት የሆነችውን አሜሪካንና የሀበሻን ውሎ የሚፈትሸውና በአዝናኝና አስቂኝ ታሪኮች  የተሞላው መጽሐፉ፤ “ወደ ቦሌ እግርህን ከማንሳትህ በፊት ትርፍና ኪሳራህን አስላ” የሚል ትልቅ ምክር መያዙንም ደራሲው ገልጸዋል።  በ160 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ150 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን “ሀሁ መጽሐፍት መደብር” በዋናነት ያከፋፍለዋል ተብሏል። ደራሲው በ20 ዓመት የአሜሪካ ቆይታቸው “መኖር አሜሪካ”ን ጨምሮ 26 መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ታውቋል።

Read 11105 times