Print this page
Saturday, 15 January 2022 21:47

ጦቢያ “ግጥም በጃዝ” የቤተሰብ ቀን ፌስቲቫል ነገ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

ጦቢያ ግጥም በጃዝ “ወደ ቤት ወደ ሀገር ቤት አንድ እንጀራ ለጎረቤት” በሚል መርህ፣ በነገው ዕለት በጊዮን ሆቴል “ግሮቭ ጋርደን ዎክ” ልዩ የቤተሰብ ቀን ፌስቲቫል ማዘጋጀቱን ገለጹ።
ፌስቲቫሉ በተለይም ከተለያዩ ዓለማት ወደ እናት ሀገራቸው የሚገቡ እንግዶችን የመቀበል ስነስርዓት ሲሆን ሁላችንም  ሰንደቃችን ጥለት በባህል ልብስ የምንደምቅበት ልዩ  የኪነ ጥበብ መድረክ ነውም ተብሏል።
ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ መናፈሻው ለእንግዶች ክፍት የሚሆን ሲሆን፣ እስከ ቀኑ 10፡00 የተለያዩ የጥበብ ድግሶች እንደሚቀርቡና ከ10-12፡00 የጦቢያ 10ኛ ዓመት  የምስረታ በዓል የመጀመሪያ ምዕራፍ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ገልጸዋል። በእለቱ ባህላዊ ምግቦችና መጠጦች፣ በመናፈሻው ከልዩ የጀበና ቡና ጋር የሚቀርብ ሲሆን ህጻናት ለእነሱ በተገነባው የመጫወቻ ቦታ ሆነው ይጫወታሉ ይዝናናሉም ተብሏል።

Read 11093 times