Tuesday, 25 January 2022 07:56

በዚህ ፈታኝ ወቅት ለአገራችን የማይበጃት!

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

አገራችን የህወሃት አሸባሪ ቡድን ከአፋር እስከ አማራና ሰሜን ሸዋ ወረራ ባካሄደበት ወቅት ከነበረው ሁኔታ በእጅጉ በተሻለ እፎይታና መረጋጋት ውስጥ ትገኛለች፡፡  
ቢያንስ በየጀንበሩ ሴት እህቶቻችንና እናቶቻችን ተገድደው አይደፈሩም፤ ወጣቶች በጅምላ አይገደሉም ፣ መሰረተ ልማቶች አይዘረፉም፣ አይወድሙም፡፡ ነገር ግን የአገራችን ህልውና መቶ በመቶ ተረጋግጧል ማለት አይቻልም፡፡
ያለ ጦርነት መኖር የማይችለው አሸባሪው የህወኃት ቡድን፤ ለሌላ ዙር ጥፋትና ወረራ ራሱን እያዘጋጀ መሆኑን እየሰማን ነው፡፡  አለፍ ገደም እያለም በሰላማዊ ህዝባችን ላይ ከባድ መሳሪያዎችን እየተኮሰ መሆኑ ይነገራል፡፡
ስለዚህም ጦርነቱ ተጠናቅቋል ብለን ትኩረታችንን ከዚህ አጥፊ ቡድን ላይ ማንሳት የለብንም። ወደተለያዩ ውዝግቦችና ክፍፍሎች እንዳንገባም መጠንቀቅ ይገባናል- አንድነታችንን ያዳክምብናልና፡፡ እናም በዚህ ፈታኝ ወቅት ለአገራችን የማይበጃትን አሉታዊ ነገሮች ልናጤን ይገባል ብዬ አምናሁ፡ ለምሳሌ፡-
የጠብና ልዩነት አጀንዳ እየጠመቁ፣ ህዝብን በሃይማኖትና በዘር እየከፋፈሉ ማጋጨት፤
ትናንሽ ቅሬታዎችንና ተቃውሞዎችን እያራገቡ፣ ሽብርና አለመረጋጋትን መፍጠር፤
የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሰበብ አስባቡ መንግስትና ህዝብን ማጋጨት፤
ትልቁን የአገር የሉአላዊነት  ጉዳይ ወደ ጎን በማድረግ፣ ከመንግስት ጋር እልህና ንትርክ ውስጥ መግባት፤
የድል አጥቢያ አርበኛ ለመሆን በሚደረግ ትንቅንቅ የአገርን ህልውና ለአደጋ ማጋለጥ፤
ለአሉባልታና ለከፋፋይ ድምጾች ጆሮ በመስጠት ከአጥፊዎች ጋር መተባበር፤ ወዘተ…
ጽዮን-ከጦር ሃይሎች


Read 458 times