Print this page
Saturday, 29 January 2022 00:00

አድማስ ዩኒቨርስቲ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት አስገመገመ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፉት 20 ዓመታት በመማር ማስተማር ሂደቱ በርካታ የተማረ ሃይል በማፍራት ግንባር ቀደም የሆነው አድማስ ዩኒቨርስቲ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ከአድማስ ዩኒቨርስቲ  ቀለምና ቅርጽ ጋር አጣጥሞ በሚሄድበት መንገድ ላይ የግምገማ መርሃ ግብር አካሂደ “curricular validation work shop” በተሰኘው በዚህ መርሃ ግበር ላይ የመንግስት ለውጥን ተከትሎ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መንግስት ለውጦችን እያደረገ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ  አንዱ ሥርዓተ ትምህርቱ  መሆኑን የአድማስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ሞላ ጸጋዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ከለውጦቹ መካከል በ3 ዓመት ይጠናቀቅ የነበረው የዲግሪ ፕሮግራም ወደ አራት ዓመት ከፍ ማለቱና አዳዲስ ኮርሶች መጨመራቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ምን ተጽዕኖ አለው? መንግስት ያስቀመጣቸው ገደቦችስ ምን ይፈጥራሉ? የጋራ አስገዳጆቹን ነገሮች ተቀብሎ በአድማስ ዩኒቨርስቲ ቅርፅና ቀለም ለማስቀጠል ምን ምን ግብአቶች ያስፈልጋሉ የሚሉት የወርክ ሾፑ ዋነኛ ማጠንጠኛ መሆናቸውን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ማክሰኞ ቀኑን ሙሉ በዋሽንግተን ሆቴል በተካሄደው በዚህ ወርክ ሾፕ ላይ የስራ ፈጣው (ኢንዱስትሪው) ተወካዮች፣ በትምህርት ላይ የሚሰሩ ኤክስፐርቶች፣ የመንግስት ባለድርሻ አካላትና የግል ዩኒቨርስቲ ተወካዪች ተሳትፈውበታል፡፡ ከወርክ ሾፑ የሚገኙ ግብአቶች ታይተውና ተገምግመው ወደ ዩኒቨርስቲው ሴኔት ከቀረቡ በኋላ ተግባር ላይ እንደሚሉም ሞላ ጸጋዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡


Read 2634 times
Administrator

Latest from Administrator