በዛጎል የመፅሀፍት ባንክና በዋልያ መፅሀፍት ትብብር ዛሬ ከቀኑ 10፡00 እስከ 12፡00 በ“ክብር” መፅሐፍ ላይ ውይይት ይካሄዳል፡፡
አራት ኪሎ ኢክላስ ህንፃ ላይ በሚካሄደው በዚህ መርሃ ግበር ላይ የደራሲ ቃልኪዳን ሀይሉ አራተኛ ሥራ የሆነው “ክብር” መፅፍ የተመረጠ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ ደራሲው ተገኝቶ ከአንባቢያን ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚስጥና የመፅሀፍ ፊርማ ስነ- ሥርዓት እንደሚያከናውን አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡ በዕለቱ ትልልቅ ደራሲያን፣የስነ ፅፍ አፍቃሪያን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ጀማሪ መጽሀፍት ይገኛሉ የተባለ ሲሆን የትውውቅና የውይይት ጊዜም እንደሚኖር ታውቋል፡፡
ደራሲ ቃልኪዳን ሀይሉ “ለምን አትቆጣም” “የነጎድጓድ ልጆች” እና “አላቲኖስ” የተሰኙ መፅሀፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን “ክብር” የተሰኘው አራተኛና አዲሱ ስራው መሆኑ አይዘነጋም፡፡ አዘጋጆቹ ፍላጎት ያለው በመርሃ ግበሩ ላይ እንዲሳተፍና ጠቃሚ ሀሳቦችን እንዲገበይ ጋብዘዋል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና