Saturday, 29 January 2022 00:00

ኮሮና አሁንም ከ616 ሚ. በላይ ተማሪዎችን አስተጓጉሏል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የፈጠረው ቀውስ በአለማችን ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉንና በአሁኑ ወቅትም ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል በመዘጋታቸው ሳቢያ በአለማችን ከ616 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ተስተጓጉለው እንደሚገኙ ተመድ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ሰሞኑን ይፋ ባደረገው አለማቀፍ ሪፖርቱ እንዳለው፣ ወረርሽኙ ተማሪዎችን ከመደበኛ ትምህርታቸው ከማሰናከሉ በተጨማሪ ለተለያዩ የአእምሮ ህመሞች፣ ለምግብ እጥረትና ለቤት ውስጥ ጥቃቶች እያጋለጠ ይገኛል፡፡ ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ሳቢያ ዕድሜያቸው 10 አመት ከሆናቸው የአለማችን ተማሪዎች መካከል 70 በመቶ ያህሉ አንድን ቀላል ቃል ማንበብም ሆነ መረዳት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፣ ከ370 ሚሊዮን በላይ ህጻናትም የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው አመልክቷል፡፡

Read 1072 times