Saturday, 29 January 2022 00:00

ዳንጎቴ ለ11ኛ ተከታታይ አመት የአፍሪካ ቁጥር 1 ባለጸጋ ተባሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ላለፉት 10 ተከታታይ አመታት የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነርነቱን ስፍራ ሳያስነኩ የዘለቁት ናይጀሪያዊው ባለጸጋ አሊኮ ዳንጎቴ፣ ዘንድሮም ክብራቸውን ማስጠበቃቸውን ፎርብስ መጽሄት ይፋ አድርጓል፡፡
ታዋቂው ፎርብስ መጽሄት ከቀናት በፊት ባወጣው የ2022 አፍሪካውያን ባለጸጎች ዝርዝር ውስጥ፣ ዳንጎቴ በ13.9 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሃብት ነው 1ኛ ደረጃን የያዙት፡፡
የደቡብ አፍሪካው የቅንጦት እቃዎች አምራች ኩባንያ ባለቤት ጆአን ሩፐርት በ11 ቢሊዮን ዶላር ሃብት የሁለተኛነት ደረጃን ሲይዙ፣ በውድ ማዕድናት ንግድ ዘርፍ የተሰማሩት ኒኪ ኦፐናይመር በ8.7 ቢሊዮን ዶላር ሶስተኛነቱን ይዘዋል፡፡
ከአንደኛ እስከ 18ኛ ያለውን ደረጃ ከያዙት የአፍሪካ ቢሊየነሮች መካከል አንድም ሴት አለመኖሩ የተነገረ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ አምስት፣ ግብጽ አምስት፣ ናይጀሪያ ሶስት፣ ሞሮኮ ሁለት ሴት ቢሊየነሮች ማስመዝገባቸውን ፎርብስ አመልክቷል፡፡


Read 1230 times