Saturday, 29 January 2022 00:00

በአመቱ ከ40 ቢሊዮን በላይ ሚስጥራዊ መረጃዎች ተሰርቀው ተሰራጭተዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው የፈረንጆች አመት 2021 ብቻ በመላው አለም ከ40 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ የተቋማትና የግለሰቦች ሚስጥራዊ መረጃዎች በመንታፊዎች ተሰርቀው በተለያዩ መንገዶች ለህዝብ መሰራጨታቸው ተነግሯል፡፡
ቴኔብል የተባለው የሳይበር ጥቃት መከላከያና ጥናት ተቋም ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳለው፣ በአመቱ በመላው አለም 1 ሺህ 825 የመረጃ ምንተፋ ድርጊቶች የተፈጸሙ ሲሆን በምንተፋ ለህዝብ የተሰራጩ መረጃዎች ብዛትም ባለፈው አመት ከነበረበት የ78 በመቶ ያህል ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡
ወደ 22 ሺህ የሚጠጉ የመረጃ ቋቶች ለጥቃት ተጋላጭ መሆናቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፣ በአመቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መረጃዎች የተዘረፉባቸው ቀዳሚዎቹ ዘርፎች የጤና እና የትምህርት ዘርፎች መሆናቸውን አብራርቷል፡፡


Read 1130 times