Print this page
Saturday, 29 January 2022 00:00

አፕል በ355.1 ቢ. ዶላር የንግድ ምልክት ዋጋ ቀዳሚው ኩባንያ ተብሏል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአዲሱ የፈረንጆች አመት 2022 ከአለማችን ኩባንያዎች መካከል በንግድ ምልክት ዋጋ አፕልን የሚስተካከለው አልተገኘም፤ ኩባንያው በ355.1 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ የ1ኛነትን ደረጃ መያዙ ተነግሯል፡፡
ብራንድ ፋይናንስ የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባለፈው ማክሰኞ ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርቱ እንዳለው፣ የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል የንግድ ምልክት ዋጋው ባለፈው አመት ከነበረበት የ35 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ነው 355.1 ቢሊዮን ዶላር የደረሰው፡፡
ሌላኛው የአሜሪካ ኩባንያ አማዞን በ350.3 ቢሊዮን ዶላር የሁለተኛነት ደረጃን ሲይዝ፣ ጎግል ኩባንያ በበኩሉ በ263.4 ቢሊዮን ዶላር ሶስተኛ ለመሆን ችሏል፡፡
በንግድ ምልክት ዋጋ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አቻ እንዳልተገኘላቸው የተነገረ ሲሆን ኩባንያዎቹ በድምሩ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር የንግድ ምልክት ዋጋ ማስመዝገባቸውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Read 2812 times
Administrator

Latest from Administrator