Print this page
Saturday, 05 February 2022 12:07

“ዳኛቸው ወርቁ ማን ነው?” የውይይትና የመታሰቢያ መርሃ ግብር ዛሬ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ህሩይ  ወ/ስላሴ የስነ-ጥበባት ማዕከል ያሰናዳው “ዳኛቸው ወርቁ ማን ነው?” የተሰኘው ውይይትና የመታሰቢያ ልዩ መርሃ ግብር ዛሬ ጥር 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ አካባቢ በሚገኘው የማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።
በዕለቱ ደራሲ ሳህለ ስላሴ ብርሃነ ማሪያም “ዳኛቸው ሰውየውን” የሚዳስሱ ሲሆን እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር) ደግሞ ደራሲው ዳኛቸው ወርቁ ምን እደሚመስል እንደሚያስቃኙና የስነጽሁፍ መምህሩ ገዛኀኝ ፀጋው (ዶ/ር) ደግሞ ገጣሚው ዳኛቸው ወርቁ ምን መልክ እንደነበረው የሚያብራሩበት ልዩ መርሃ ግብር መሆኑን የማእከሉ ሃላፊዎች አስታውቀዋል። በዚህ መርሃ ግብር ላይ መሳተፍ የሚፈልግ የኮቪድ 19ን ፕሮቶኮል ጠብቆ እንዲታደምም ጥሪ ቀርቧል።

Read 11387 times
Administrator

Latest from Administrator