Print this page
Saturday, 05 February 2022 12:27

ግብጽ በ2 ሳምንት የ4.1 ቢ. ዶላር የጦር መሳሪያ ግዢ ፈጽማለች

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካ ጋር የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ግዢ ስምምነት የፈጸመው የግብጽ መንግስት፤ ባለፈው ማክሰኞ ደግሞ ከደቡብ ኮርያ ጋር ተጨማሪ የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ግዢ ስምምነት መፈጸሙን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡
የደቡብ ኮርያው ፕሬዚዳንት ሞን ጃኢን ጽህፈት ቤት ከሴኡል ባለፈው ማክሰኞ ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው፤ የአገሪቱ መንግስት ኬናይን የተባሉ ዘመናዊ የጦር ታንኮችን ለመሸጥ ከግብጽ ጋር ስምምነት ከመፈጸሙ ውጪ ምን ያህል ታንኮችን ለመሸጥ ማቀዱን አልገለጸም፡፡
የጦር መሳሪያ ስምምነቱ በደቡብ ኮርያ መዲና በተፈጸመበት ወቅት የግብጹ የመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሞሃመድ ዛኪ መገኘታቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ የደቡብ ኮርያው ፕሬዚዳንት ከሁለት ሳምንታት በፊት በግብጽ ጉብኝት ማድረጋቸውንና ከግብጹ አቻቸው አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጋር መገናኘታቸውንም አስታውሷል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ሳምንት ለግብጽ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ለመሸጥ ስምምነት መፈጸሙን እንዳስታወቀ ያስታወሰው ዘገባው፤ ግብጽ በሁለት ሳምንታት ውስጥ የፈጸመችው የጦር መሳሪያ ግዢ 4.1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱንም አመልክቷል፡፡

Read 2019 times
Administrator

Latest from Administrator