Print this page
Wednesday, 09 February 2022 10:37

አሜሪካ በሶማሊያ መሪዎች ላይ የቪዛ ዕቀባ ልትጥል ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የአሜሪካ መንግሥት በሶማሊያ ዴሞክራሲ እክል ፈጥረዋል ያላቸው ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ ማዕቀብ እንደሚጥል አስታወቀ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ የቪዛ ዕቀባው በተቃዋሚዎች ላይ ኃይል በሚጠቀሙ መሪዎች ላይም ተፈጸሚ ይሆናል ብለዋል።
ይህ የአሜሪካ መንግሥት የቪዛ ማዕቀብ የተሰማው ሶማሊያ አጠቃላይ ምርጫ ማካሄድ ከነበረባት ጊዜ አንድ ዓመት መዘግየቷን ተከትሎ ነው።
የፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ የሥልጣን ዘመን ካበቃም አንድ ዓመት አስቆጥሯል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ምክንያታዊ ያልሆነ እስር በሚፈጽሙ፣ በጋዜጠኞችና በተቀዋሚዎች ላይ ጫና በሚያሳድሩና በምርጫ ሂደት ላይ መሰናክል በሚፈጥሩ ላይ የቪዛ ማዕቀቡ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ይህ የቪዛ ማዕቀብ በባለሥልጣናቱ የቅርብ የቤተሰብ አባላት ላይም እንደሚጣል አንቶኒ ብሊንከን ሶማሊያን በሚመለከት ባወጡት መግለጫ ላይ አመልክተዋል።
"የሶማሊያ ብሔራዊና የፌደራል መንግሥቱ አመራሮች ተአማኒና ግልጽ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነበረባቸው" ብለዋል ብሊንከን።
አሜሪካ በሶማሊያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለመተባበር ዝግጁ መሆኗንም ብሊንከን ጠቅሰዋል።
ፈርማጆ የፓርላማ እንዲሁም የፕሬዚዳንታዊ ምርጫን አራዝመው ሥልጣን ላይ ለመቆየት መወሰናቸው ሶማሊያን ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ከከተታት ሰነባብቷል።
ሶማሊያ የፓርላማ ምርጫን እስከ መጪው የካቲት 27 አከናውና ወደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ትገባለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Read 5486 times
Administrator

Latest from Administrator