Saturday, 12 February 2022 11:45

ኤምሬትስ ወደ ዱባይ በጋራ ለሚጓዙ 25 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  በአለማችን ከሚገኙ ትላልቅ አየር መንገዶች አንዱ የሆነው ኤምሬትስ፤ እስከ የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር በጋራ ዱባይን ለመጎብኘት ትኬት ለሚቆርጡ ተጓዦች  ልዩ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ይህ ልዩ ቅናሽ ሁለትና ከዚያ በላይ በመሆን ከኤምሬትስ ዋና ድረገጽ ላይ ደርሶ መልስ የኢኮኖሚና የቢዝነስ ትኬት ከጥር 16 ጀምሮ እስከ የካቲት 6 ድረስ ለሚቆርጡ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በጉዞ ወኪሎችና የጥሪ ማዕከላት እንዲሁም በኤምሬትስ ቆንፅላ ቢሮዎች ለሚገዙ ትኬቶችም ቅናሹ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ከአዲሱ ልዩ ቅናሽ በተጨማሪ ከኤምሬትስ ጋር ወደ ዱባይ በመብረር በርካታ ጥቅሞችን ማትረፍ ይችላሉ ተብሏል፡፡
ነፃ የኤክስፖ መግቢያ ከኤምሬትስ፡
እጅግ ተፈላጊ የሆነውና በጉጉት የሚጠበቀው የዱባይ 2020 ኤክስፖ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2014 ድረስ የሚቆይ በመሆኑ ወደ ዱባይ ለመጓዝ እጅግ ጥሩ ጊዜ ላይ ነን፡፡
እስከ ኤክስፖ ማብቂያ ድረስ ባሉት ቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ወደ ዱባይ የሚጓዙ የኤምሬትስ ደምበኞችም ነፃ የመግቢያ ትኬት የሚያገኙ ይሆናል። ስለዚህ እድል የበለጠ መረዳት ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠርያ በመጫን የበለጠ ማወቅ ይቻላል፡፡ dedicated offer page
ማይ ኤምሬትስ ፓስ- ኤክስፖ፡
እስከ መጋቢት 22 ድረስ ወደ ዱባይ የሚጓዙም ሆነ በዱባይ የሚያልፉ ደንበኞች ከተማዋን በትንሽ ወጪ ብቻ መጎብኘት የሚችሉበት አጋጣሚ ተመቻችቷል። የኤምሬትስ ቦርዲንግ ፓስ በማሳየት ብቻ ከ500 በላይ የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ ሱቆች፣ ምግብ ቤቶችና መዝናኛ ቦታዎችን መጎብኘትና በቅናሽ መጠቀም ይችላሉ፡፡
በአንድ ደቂቃ አንድ ማይል ያግኙ፡
እስከ መጋቢት 22 ድረስ የኤምሬትስ ደንበኞች በዱባይ በሚኖራቸው እያንዳንዷ ደቂቃ አንድ የስካይዋርድ ማይል ያገኛሉ። በዚህ ፕሮግራም ከመጋቢት 22 በፊት የተመዘገቡ ነባርም ሆነ አዲስ የኤምሬትስ ስካይዋርድ አባላት የዚህ ጥቅም ተካፋይ መሆን የሚችሉ ሲሆን እስከ 5000 ድረስ የስካይዋርድ ማይልስ ሊያገኙ ይችላሉ።  ይህ እድል የዱባይ 2022 ኤክስፖ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ  ለማንኛውም የዱባይ ጉዞ የኤምሬትስ ትኬት ላይ የሚኖር ይሆናል፡፡

Read 9917 times