Saturday, 12 February 2022 11:50

የአሜሪካ ም/ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ፣ በኢትዮጵያ ላይ የብድር ማዕቀብ እንዲጣል የሚደነግግ የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ፣  ኢትዮጵያን በተመለከተ አዲስ ረቂቅ ህግ ያወጣ ሲሆን ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ግጭትን እያባባሱ በሚገኙ አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚያዝ ነው ተብሏል።
“የኢትዮጵያ የመረጋጋት፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ህግ” በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ረቂቅ ህግ፤ በዋናነት በአሜሪካ የኒውጀርሲና ካሊፎርኒያ ግዛት ተወካዮች በጋራ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ለሀገሪቱ መንግስት የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ እንዲቋረጥና አሜሪካን  ለኢትዮጵያ የምታደርገው የደህንነትና ፀጥታ ትብብር እንዲቆም ይደነግጋል።
በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የፀደቀው ረቂቅ ህጉ በቀጣይ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀ ብቻ ነው ተግባራዊ የሚደረገው፤ ህጉ ለኢትዮጵያ ምንም አይነት እርዳታም ሆነ ብድር እንዳይሰጥ የሚጠይቅ ነው።
 ይህ ረቂቅ ህግ በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ድርድሩን በማይቀበሉና ግጭቱ እንዳይቆም በሚፈልጉ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት  በሚፈጽሙ፣ መከራን በሚያስፋና በማናቸውም ጠብ አጫሪ ወገኖች የጦር መሳሪያ በሚሸጡ አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ያስችላል ተብሏል።
ለሰብአዊ እርዳታዎች ካልሆነ በስተቀር እንደ የአለም ባንክና  አለማቀፍ የገንዘብ ድርጅትን የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት ለኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት  የገንዘብ እርዳታዎችንም ሆነ ብድሮችን እንዳይሰጡ፤ የአሜሪካ መንግስትም ጫና እንዲያደርግ ረቂቅ ህጉ ይጠይቃል።
በዚህ ረቂቅ ህግ ላይ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብአዊ ወንጀሎች ጦር ወንጀልና ዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ መካሄድ አለመካሄዱን መርምሮ እንዲያሳውቅ፤ ግጭቱን የሚያባብሱ ማናቸውም አካላት ተጠያቂነት ያለባቸው መሆኑን እንዲያውቁ እንዲደረግም በረቂቅ ህጉ ተመልክቷል።



Read 10239 times