Print this page
Saturday, 12 February 2022 12:34

ኤለን መስክና ጄፍ ቤዞስ በአንድ ቀን ብቻ 7 ቢሊዮን ዶላር አግኝተዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ፌስቡክና ኢንስታግራም በመላ አውሮፓ ሊዘጉ ይችላል ተባለ

               ሁለቱ የአለማችን ቢሊየነሮች ኤለን መስክና ጄፍ ቤዞስ ባለፈው ማክሰኞ በተመዘገበ የአክሲዮን ገበያ ዋጋ ጭማሪ፣ እያንዳንዳቸው ተጨማሪ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ሃብት ማግኘታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል፡
ቁጥር አንዱ የአለማችን ቢሊየነር ኤለን መስክ በዕለቱ ተጨማሪ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ሃብት በማፍራት አጠቃላይ ሃብቱን ወደ 238 ቢሊዮን ዶላር ማሳደጉን የጠቆመው የብሉምበርግ ዘገባ፣ ለሃብቱ ጭማሪ ምክንያት የሆነው የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ የአክሲዮን ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ነው ብሏል፡፡
የአማዞኑ መስራች የ58 አመቱ ጄፍ ቤዞስ በበኩሉ ኩባንያው ማክሰኞ ዕለት የ2.2 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱንና አጠቃላይ የገበያ ዋጋው ወደ 1.64 ትሪሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን ተከትሎ መስራቹ ቤዞስ ተጨማሪ 3.5 ቢሊዮን ዶላር በማፍራት አጠቃላይ ሃብቱን ወደ 186 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ፣ ታዋቂዎቹን የማህበራዊ ድረገጾች ፌስቡክና ኢንስታግራም የሚያስተዳድረው ሜታ ኩባንያ፣ በአውሮፓ አገራት ከሚወጡ የማያሰሩ የመረጃ ህጎችና ገደቦች ጋር በተያያዘ፣ ሁለቱንም ድረገጾች በመላ አውሮፓ ሙሉ ለሙሉ ሊዘጋ እንደሚችል ከሰሞኑ አስጠንቅቋል፡፡
የአውሮፓ አገራት የሚያወጧቸው የመረጃ ህጎች ክልከላ የሚበዛባቸውና የማያሰሩ በመሆናቸው አገልግሎቱን ሙሉ ለሙሉ ሊያቋርጥ እንደሚችል የገለጸው ሜታ፤ በቅርቡ አዳዲስ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍም አስታውቋል፡፡



Read 1208 times
Administrator

Latest from Administrator