Saturday, 12 February 2022 12:35

የቀድሞው የቡርኪናፋሶ መሪ በቶማስ ሳንካራ ግድያ 30 አመት እስር ተጠየቀባቸው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በአፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ሰዎች አንዱ በሆነው ቶማስ ሳንካራ ግድያ እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩት  የቀድሞው የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓዎሬ በ30 አመት እስር እንዲቀጡ የአገሪቱ አቃቤ ህግ መጠየቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እ.ኤ.አ በ1987 በተፈጸመበት ግድያ በ37 አመቱ ከዚህ አለም በሞት የተለየውን የቀድሞው የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ቶማስ ሳንካራ ጉዳይ በመመርመር ላይ የሚገኘው የጦር ፍርድ ቤት፣ ግድያውን ተከትሎ በተደረገ መፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡትና ከ27 አመታት ስልጣን በኋላ በ2014 በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን ወርደው አሁን በአይቬሪኮስት በስደት ላይ የሚገኙትን ብሌስ ኮምፓዎሬ በ30 አመት እስር እንዲቀጣ አቃቤ ህግ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረቡን ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡
ኮምፓዎሬ በሳንካራ ግድያ እጄ የለበትም ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው የተነገረ ሲሆን፣ ግድያው ከተፈጸመ ከ34 አመታት በኋላ በ12 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ የጀመረው የአገሪቱ የጦር ፍርድ ቤት፣ በቅርቡ ውሳኔውን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክቷል፡፡


Read 2216 times