Print this page
Tuesday, 15 February 2022 00:00

‹ፓዎር ኦፍ ዘ ዶግ› ለኦስካር 12 ጊዜ በመታጨት ቀዳሚ ሆኗል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   ለ94ኛ ጊዜ የሚካሄደው የኦስካር አካዳሚ ሽልማት ዕጩዎች ባለፈው ማክሰኞ ይፋ የተደረጉ ሲሆን፣ በኔትፍሊክስ አማካይነት ለእይታ የበቃው ‹ፓዎር ኦፍ ዘ ዶግ› 12 ጊዜ በመታጨት በብዛት የታጨ ቀዳሚው ፊልም ሆኗል፡፡
‹ፓዎር ኦፍ ዘ ዶግ› ምርጥ ፊልምና ምርጥ ዳይሬክተርን ጨምሮ 12 ጊዜ ለዘንድሮው ኦስካር ሽልማት በመታጨት ነው 1ኛ ደረጃን የያዘው፡፡
በዋርነር ብሮስ ኩባንያ ለእይታ የበቃው ‹ዱኒ› በበኩሉ 10 ጊዜ በመታጨት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፣ ቤልፋስት እና ዌስት ሳይድ ስቶሪ እያንዳንዳቸው 7 ጊዜ በመታጨት ሶስተኛ ደረጃ መያዛቸው ተነግሯል፡፡
የዘንድሮው ኦስካር ሽልማት ስነስርዓት በመጋቢት ወር መጨረሻ በዶልቢ ቲያትር በደማቅ ሁኔታ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
‹ዘ ትራጄዲ ኦፍ ማክቤዝ› በተሰኘው ፊልም ባሳየው ድንቅ ትወናው ለዘንድሮው ኦስካር በምርጥ ተዋናይነት ዘርፍ ለሽልማት የታጨውና በአጠቃላይ ለ10ኛ ጊዜ ለኦስካር የታጨው ዴንዝል ዋሽንግተን ለኦስካር በብዛት በመታጨት ቀዳሚው ጥቁር የፊልም ተዋናይ በመሆን ታሪክ መስራቱ ተነግሯል፡፡

Read 2793 times
Administrator

Latest from Administrator