Print this page
Wednesday, 16 February 2022 00:00

ኮሮናን በቁጥጥር ስር ለማዋል 23 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአለማችን በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ400 ሚሊዮን አልፏል

             በመላው አለም የተመዘገበው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ባለፈው ረቡዕ ከ400 ሚሊዮን ማለፉ የተነገረ ሲሆን፣ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በቁጥጥር ስር ለማዋልና በሽታው አለማቀፍ የጤና ቀውስ መሆኑ እንዲያበቃ ለማድረግ 23 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው የአለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
የተጠቀሰው ገንዘብ ለድሃ አገራት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መሳሪያዎች፣ ህክምናና ክትባቶች መግዣ እንደሚውል የገለጸው ድርጅቱ፤ 55 ሃብታም የአለማችን አገራት ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስፈልገውን ገንዘብ በመለገስ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ባለፈው ረቡዕ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ድሃ አገራት ክትባትም ሆነ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን በበቂ መጠን እያገኙ አይደለም ያለው ድርጅቱ፤ በመላው አለም ከተሰራጩት 4.7 ቢሊዮን ያህል መመርመሪያ መሳሪያዎች ለድሃ አገራት የደረሱት 0.4 በመቶው ብቻ መሆናቸውንም አክሎ ገልጧል፡፡ በመላው አለም በቫይረሱ ሳቢያ ለሞት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር በዚህ ሳምንት ከ5.8 ሚሊዮን ማለፉ የተነገረ ሲሆን፣ በአለማቀፍ ደረጃ የተሰጡ ክትባቶች ቁጥርም ከ10 ቢሊዮን እንደሚበልጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡


Read 6321 times
Administrator

Latest from Administrator