Tuesday, 22 February 2022 00:00

ሴቶች የፕሮስቴት ካንሰር ይይዛቸዋልን?

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

     ሴቶች የፕሮስቴት ካንሰር ይይዛቸዋል ተብሎ ስጋት ከሚጣልበት ደረጃ ላይ የሚደርስ ችግር የለም ለማለት ይቻላል ይህ ሲባል ግን ጭርሱንም ስጋት የለም ለማለት አይደለም፡፡ አልፎ አልፎ በጣም ጥቂት በሚባል ደረጃ የሚሰማ የታማሚዎች ሪፖርት ቢኖር እንኩዋን እንደ ወንዶች የፕሮስቴት እጢ ኖሮአቸው ሳሆን Skene’s glands በተባሉት ላይ የሚደርስ ሲሆን እሱም 0.003 ከመቶ ከሚባል ደረጃ መሆኑን ቀደም ያለ ጥናት ያሳያል፡፡ ይህም በሴቶች የሽንት መሽኛ አካባቢ የሚከሰት የካንሰር አይነት ነው፡፡ ይህ የካንሰር ሕመም እንደ ሽንት መሽኛ ያሉ በቅርብ የሚገኙ የሰውነት ክፍሎች አካባቢም ሊፈጠር ይችላል፡፡ Skene’s glands  የሚባሉት እጢዎች በሴት ብልት ከፊት ለፊት በኩል በሽንት መሽኛ ቱቦ በግራና በቀኝ በኩል የሚገኙ ናቸ ው፡፡ አገልግሎታቸውም ሽንት ከተሸና በሁዋላ አካባቢው ንጹህ እንዲሆንና በወሲብ  ግንኙነት ወቅት አካልን ለማለስለስ የሚረዱ ናቸው፡፡  Bottom of Form ሴቶች እንደ ወንዶች ፕሮስቴት ተብሎ የሚጠራ አካል የላቸውም፡፡ በሴቶች የውስጥ አካል ሽንት መሽኛ ቱቦ በግራና በቀኝ በኩል የሚገኙት እጢዎች የሴቶች ፕሮስቴት ወይንም Skene’s glands ተብለው ይጠራሉ። እነዚህ እጢዎች ነጭ ፈሳሽ ከሚወጣበት አካል ጀምሮ እስከ ሽንት መሽኛ መስመር ድረስ ወይም በተለይም በአንዳንድ ሴቶች ከዚያ በላይ እስከ ወሲብ ማነቃቂያ አካል ያሉ ወይንም ከብበው የሚገኙ ናቸው ፡፡
የፐሮስቴት ካንሰርን የሚያመጣው ምንድነው?
ምንም እንኩዋን ፐሮስቴት የሚመጣው በዚህ ምክንያት ነው ለማለት ባይቻልም በህክምናው ዘርፍ ግን በመንስኤነት ተጠቃሽ የሆኑ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለምሳሌም በተመረዘ ወይንም ኢን ፌክሽን ባለው ሽንት ምክንያት የተፈጠረ ባክቴሪያ ወይንም ኢንፌክሽን ወደ ፕሮስቴት ቱቦዎች ተመልሰው የሚፈሱ ከሆነ በህክምናው አገልግሎት በካቴቴር ወደ ውጭ ካልተወገደ በስተቀር ለህመሙ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ የሽንት መሽኛ አካል ወይንም መስመር ጤናማ አለመሆን ለህመሙ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ ጥናቶች ይዘግባሉ ይላል በምን ጭነት የተጠቀምነው ሜዲካል ኒውስ። በእርግጥ በቀጥታ የፕሮስቴት ካንሰር ተብሎ የሚገለጸው በወንዶች ተፈጥሮ ሲሆን በሴቶች ግን ያልተለመደና ብዙም የማያጋጥም እንዲሁም እንደ ፕሮስቴት ካንሰር የሚቆጠረውም የSkene’s glands ካንሰር ነው፡፡  
ፕሮስቴት መኖሩን ጠቋሚ ሊሆኑ የሚችሉ አምስት ምልክቶች
ቶሎ ቶሎ ሽንት የመሽናት ፍላጎት፤
በእንቅልፍ ጊዜ ቶሎ ቶሎ ለሽንት መነሳት፤
በሽንት ውስጥ ወይንም በፈሳሽ ውስጥ ደም መታየት፤
ሽንትን ለመሽናት ህመም መሰማት ወይንም የማቃጠል ስሜት፤
ሸንት መሽናት አለመቻል፤
በግንኙነት ወቅት ፈሳሽ ለማፍሰስ መቸገር፤
የሴቶች ፕሮስቴት ካንሰር ስርጭት
የሴቶች ፕሮስቴት ካንሰር ተብሎ የሚጠቀሰው በጣም ጥቂት ወይንም አልፎ አልፎ የሚታይ ሕመም ነው፡፡ ቀደም ሲል የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው እ.ኤ.አ  በ1994 የሴቶች የፕሮስቴት ካንሰር ሕመም ተብለው ከቀረቡት ውስጥ 0.003 ከመቶ ያህል ብቻ የሴቶች የሽንት መሽኚያ መስመሮች ወይንም ብልት አካባቢ የደረሱ ህመሞች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2017 የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው የሴቶች ፕሮስቴት ካንሰር ተብሎ የሚገለጸው የካንሰር አይነት ባያጋጥምም በሴቶች ብልት አካባቢ ሌሎች ተጠቃሽ የሆኑ የካንሰር አይነቶች በስፋት መስተዋላቸው ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ጥናት አቅራቢዎች እንደሚመክሩትም በሴቶች ብልት አካባቢ የሚከሰትን ካንሰር በሚመለከት ወደፊትም የተሻለ ጥናት ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው እንደ Medical news today newsletter ዘገባ፡፡
የሴቶች ፕሮስቴት ካንሰር የሚባለው ሕመም እንደወንዶች የፕሮስቴት እጢ ኖሮ ሳይሆን Skene’s gland በተባሉ እጢዎች ላይ በሚደርስ ሕመም የሚከሰት ሲሆን ይህም በእጅጉ ተራርቆ ወይንም በቁጥር ውስን በሆኑ ሴቶች ላይ መከሰቱ ለዶክተሮችም በንቃት የማይከ ታተሉት ወይንም የሕመሙን ምንነት በፍጥነት የማይገምቱት ወይንም ይደርሳል ብለው የማይገምቱት አድርጎታል ይላል መረጃው፡፡ በታማሚዎች ላይ የሚታየው የህመም ስሜት ቲዩመር የተባለ እጢ ሊሆን ይችላል የሚል ግምትም ሊኖር ይችላል። Skene’s glands የተባሉት እጢዎች የካንሰር ሕመም ሲገጥማቸው የሴት ፕሮስቴት ካንሰር በሚባል ህመማቸው የሚገለጸው እጢዎች በሚያመጡት ትኩሳትና እብጠት ምክንያት ቱቦአቸው ሊዘጋ ይች ላል፡፡ ይህ ሁኔታ ብዙም የተለመደ ባይሆንም ሊከሰት የሚችለው ግን ሰዎች እድሜአቸው በሰላሳዎቹ ወይንም በአርባዎቹ ውስጥ ሲሆን ነው፡፡ ይህ ሕመም ለመከሰቱም እንደማሳያ የሚጠቀ ሱት፡-
በወሲብ ግንኙነት ጊዜ ወይንም ሽንትን ሲሸኑ ሕመም መሰማት፤
ከብልት የሚፈስ ያልተለመደ ፈሳሽ፤
የተደጋገመ የሽንት መስመር ኢንፌክሽን፤
ሽንት ለመሽናት መቸገር፤ ናቸው፡፡
አብዛኞቹ ዶክተሮች የሴቶች ፐሮሰቴትን በሽንት መስመር ላይ እንደሚከሰት ኢንፌክሽን ይቆጥሩታል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን ይህ ኢንፌክሽን የ Skene’s glands መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም የህክምና እርዳታው በተለያዩ መንገዶች መሰጠት የሚገባው ሲሆን ሕክምናው የሚሰጠው በሽንት መሽኛ እና የሽንት መስመር ላይ ከሚደርሰው ኢንፌክሽን ጋር ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ይሆናል፡፡ በሌላም በኩል በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ በሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ምክንያት የሴቶች ፕሮስቴት ሊስፋፋ ይችላል፡፡ ለምሳሌም ጎኖሪያ የሚባለው ኢንፌክሽን ከብልት አካባቢ ወደ Skene’s glands, ሊተላለፍ ይችላል፡፡
Skene’s glands የተባሉት እጢዎች የካንሰር ሕመም ሲገጥማቸው የሴቶች ፕሮስቴት ካንሰር ተብለው እንደሚጠቀሱ ከላይ የተመለከትናቸው ነጥቦች ያሳያሉ፡፡ የዚህም ምክንያት እነ ዚህ እጢዎች ልክ እንደወንዶቹ በተመሳሳይ enzymes ወይንም (በሰውነት ውስጥ ያለውን የኬሚካል እንቅስቃሴ ፍጥነት እንዳይቀንስ የሚያደርግ) አስፈላጊ ነገርን ስለሚያመርት ነው፡፡ ነገር ግን ፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ሲሆን በሁለተኛነት ደረጃ የሚመደብ በከፍተኛ ሁኔታ ወንዶች ላይ የሚከሰት የካንሰር ሕመም ሲሆን የሴቶች ፕሮስቴት ካንሰር ግን ብዙም የማይ ጠቀስ በጣም ትንሽ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የሚታመሙበት ነው፡፡ ሴቶች እንደወንዶች ፕሮስቴት የሚባል እጢ የሌላቸው ሲሆን እንደፕሮስቴት ካንሰር የሚቆጠረው በብልት አካባቢ በሽንት መስመሮች በግራና በቀኝ በኩል የሚታዩ Skene’s glands, በካንሰር መያዝ ነው፡፡ በእነዚህ እጢዎች የሚከሰተውን የካንሰር ሕመም ለማጥናትም ሆነ ለመመርመር አስቸጋሪ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ በአካባቢው የሚሰማው ሕመም እየሰፋ መሄዱ ከሌሎች ሕመሞችም ጋር ሊያያዝ ይችላል የሚል ግምት ስላለ የሽንት መሽኛ ቱቦዎች ሊጎዱ ይች ላሉ፡፡
በስተመጨረሻም መረጃው አንድ ጥያቄ ያነሳል፡፡ በእርግጠኝነት ሴቶች የፕሮስቴት ካንሰር ይይዛቸዋልን የሚል ነው ጥያቄው፡፡ መልሱም አዎን ይይዛቸዋል ወይንም የለም አይይዛቸውም የሚል ይሆናል፡፡ የለም አይይዛቸውም ለሚለው መልስ ምክንያቱ ፕሮስቴት የተባለው እጢ በወንዶች ላይ ያለ ተፈጥሮአዊ አካል ሲሆን በሴቶች ላይ ግን አለመኖሩ ነው፡፡ አዎን የፕሮስቴት ካንሰር ሴቶችንም ይይዛል ለሚለው መልስ ደግሞ ሴቶች በብልታቸው ወይንም በሽንት መስመሮቻቸው አካባቢ Skene glands የሚባሉ እጢዎች ያሉአቸው ሲሆን እነዚህ እጢዎች በካንሰር ሕመም ሊጠቁ ስለሚችሉ የዚህም ውጤት በሴቶች ሽንት መቋጠሪያ ፊኛ፤ የሽንት ማስወገጃ መስመሮች፤ ባጠቃላይም በስነተዋልዶ ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ሴቶች የፕሮስቴት ካንሰር እንደያዛቸው ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
የሴቶች በፕሮስቴት ካንሰር ሕመም መያዝ አለመያዝ አነጋጋሪ ቢሆንም በSkene glands አማካኝነት የሚከሰተው ካንሰር የሚያሳየውን ምልክት ትኩረት እንዲደረግበት ለንባብ ብለናል፡፡
ሽንትን ቶሎ ቶሎ መሽናት፤ በመሽናት ጊዜ ሕመም መሰማት፤ በታችኛው የዳሌ አካባቢ ሕመም መሰማት፤ በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ ሕመም መሰማት፤ እና የወር አበባ ኡደት መዛባት የመሳሰሉት እንደምልክት ሊቆጠሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህ እና ተመሳሳይ ምልክቶች ሲታዩ በፍጥነት የህክምና ባለሙያን ማማከር ተገቢ ነው።

Read 8900 times