Print this page
Saturday, 19 February 2022 12:55

በዕድሜ አንጋፋው አፍሪካዊ መሪ የ89ኛ አመት ልደታቸውን አከበሩ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ያሉ 2ኛው አፍሪካዊ መሪ ናቸው

                  በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ ከሚገኙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች መካከል በዕድሜ አንጋፋው፣ በስልጣን ላይ ለረጅም ጊዜ በመቆየት ደግሞ ሁለተኛው ሰው የሆኑት የካሜሮኑ ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ፤ ከሰሞኑ የ89ኛ አመት ልደት በዓላቸውን በደማቁ ማክበራቸው ትችት አስከትሎባቸዋል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ልደት ባለፈው እሁድ ከመኖሪያ ቤታቸው በተጨማሪ በመንግስት ወጪ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ስነስርዓቶች መከበሩን የዘገበው አፍሪካን ኒውስ፤ ደጋፊዎቻቸው ተጨማሪ እድሜ ሲመኙላቸው ተቃዋሚዎች ደግሞ ከስልጣን የሚለቁበት ቀን እንዲቀርብ ተመኝተውላቸዋል፡፡
የአገሪቱ መንግስት ወጣቶችን ሰብስቦ በመዲናዋ ያውንዴ የፕሬዚዳንቱን ልደት በደመቀ ሁኔታ ቢያከብርም፣ ተቃዋሚዎች ግን ወጣቶቹ የ5 ዶላር አበል ተከፍሏቸው እንጂ ሰውዬውን ወድደው ልደቱን እንዳላከበሩ እየተናገሩ ነው፡፡
እ.ኤ.አ ከ1975 አንስቶ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉትና ከ1982 ወዲህ ደግሞ በፕሬዚዳንትነት በማገልገል ላይ የሚገኙት ፖል ቢያ፤ በ2008 የአገሪቱን ህገመንግስት የሁለት ዙር የስልጣን ዘመን ህግ አሻሽለው ስልጣን በማራዘማቸው ከተቃዋሚዎች ትችት ሲሰነዘርባቸው ቢቆይም፣ ምንም ሳይመስላቸው ልደታቸውን ማክበራቸው ተነግሯል፡፡
በስልጣን ላይ ካሉ የአፍሪካ መሪዎች መካከል ቢያን ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ በመቆየት የሚበልጧቸው ብቸኛው ሰው፣ እ.ኤ.አ በ1979 የያዙትን ስልጣን ሙጥኝ ብለው ዘመናትን የዘለቁት የኢኳቶሪያል ጊኒው አቻቸው ኦቢያን ንጉኤማ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡


Read 2736 times
Administrator

Latest from Administrator