Sunday, 20 February 2022 00:00

በ”ፍቅረኛሞች ቀን” ብቻ ከአበባ ሽያጭ 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)


               በዘንድሮው የቫላንታይን ዴይ (የፍቅረኛሞች ቀን ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከላከችው የአበባ ሽያጭ 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች።
ከኢትዮጵያ አበባ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማህበር የተገኘ መረጃ እንደሚያለክተው፤ በዘንድሮው  የቫላንታይን ዴይ (የፍቅረኞች ቀን) አገራችን 3ሺ ቶን አበባ ወደ ውጪ በመላክ 55 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። ይህ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በዋጋም በመጠንም ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ዘንድሮ የአበባ ዋጋ ከአምናው የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
ዘንድሮ ከፍተኛ የአበባ ምርት ወደ ውጪ አገር በመላክ ከቀደሙት አመታት የተሻለ ገቢ ለማግኘት የተቻለበት ምክንያት በርካታ አገራት በአውሮፓ ባጋጠመው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት ብዙ አበባ አምራቾች የሚጠበቀውን ያህል ምርት አምርተው ለመላክ ባለመቻላቸው የኮቪድ ወረርሽኝ በአበባ ምርት ላይ ባሳደረው ጉልህ ተፅዕኖ እንዲሁም በአበባ መላኩ ሂደት የካርጎ ችግር በማጋጠሙ ነው ተብሏል።
ከቫላንታይን ዴይ ጀምሮ ያሉት ጊዜያት በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የተለያዩ ቀኖች ማለትም የእናቶች፣ የአባቶችና የሴቶች ቀን እየተባሉ የሚከበሩ ቀናት ያሉበት ጊዜ በመሆኑና ከፍተኛ የአበባ ሽያጭ የሚከናወንባቸው ቀናት በመሆኑ ኢትዮጵያ ከአበባ ምርት ሽያጭ የምታገኘው ገቢ እየጨመረ እንደሚሄድም ተጠቁሟል።
በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን ኢትዮጵያ የአበባ ምርቶቿን በብዛት የላከችው ወደ ኔዘርላንድ፣ አንግሊዝ፣ ጀርመንና ጣሊያ እንዲሁም ሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ጃፓን፣ ኮሪያና አውስትራሊያም ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ወደ ውጪ ከላካቸው የአበባ ምርት 530 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷ ታውቋል።


Read 9328 times Last modified on Sunday, 20 February 2022 15:21