Print this page
Sunday, 20 February 2022 00:00

ዓለማቀፉ ተቋም ያጋለጠው የህወኃት የጦር ወንጀል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

 • ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከል የንፁሃን ግድያና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈፅመዋል
 • እጃቸውን ወደ ኋላ ታስረው በጅምላ የተገደሉ ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል ተብሏል
 • የ29 ዓመት ወጣት በአራት የህወኃት ወታደሮች ለ15 ሰዓታት ያህል ተደፍራለች
                 
             የህወኃት ታጣቂ ሃይሎች የአማራ ክልል ላይ ወረራ በመፈፀም የተለያዩ አካባቢዎችን ተቆጣጥረው በቆዩባቸው ጊዜያት በክልሉ  ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ በርካታ ንፁሃን ሰዎችን ሆን ብለው መግደላቸውን፤ ሴቶችና ታዳጊዎችን አስገድደው በቡድን መድፈራቸውንና የህዝብና የግል ንብረቶችን ማውደማቸውን አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሞኑን  አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
ተቋሙ በሪፖርቱ እንደገለፀው፤ የህወኃት ታጣቂ ሃይሎች በጭና፣በቆቦና በአካባቢው በሚገኙ ከተሞች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ያደረሱት  አካባቢውን ተቆጣጥረው በቆዩባቸው ጊዜያት በተለይም ከነሐሴ 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 2014 ዓ.ም መጀመሪያ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ነው፡፡ ታጣቂዎቹ ቆቦ ከተማን ለመቆጣጠር ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት፣ ከታጣቂ የከተማዋ ነዋሪዎችና ከአማራ ሚሊሻ ሃይሎች ከፍተኛ መገዳደር ገጥሟቸው የነበረ ሲሆን ከተማዋን በተቆጣጠረበት ወቅትም በእነዚህ ታጣቂ  የከተማዋ ነዋሪዎችና የሚሊሻ ሃይሎች ላይ ከፍተኛ የበቀል እርምጃ መውሰዳቸውን የአምነስቲ ሪፖርት ያመለክታል፡፡
የተቋሙ ሪፖርት እንደሚለው፤ በሰሜን ምስራቅ አማራ ክልል በምትገኘው የቆቦ ከተማ የህወኃት ታጣቂ ቡድኑ ቀድም ሲል በታጣቂ ነዋሪዎች የደረሰበትን ሽንፈት ለመቀበል ያልታጠቁ ንፁሃንን ሰዎችን በጅምላ ረሽኗል፡፡ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው ፊት ለፊት ተደርድረው ከተረሸኑ የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ግራ ትከሻውን ተመትቶ ከአስክሬኖቹ መሃል ተኝቶ በህይወት የተረፈውን ግለሰብ ምስክርነት መቀበሉን ሪፖርቱ ይጠቁማል።  “ከእነ ጎረቤቶቻችን ከቤታችን ደጃፍ እንደተደረደርን መተኮስ ጀመሩ። ወንድሜ ታደሰ ተመትቶ ወደቀ። በዚህ ወቅት ሌላኛው ወንድሜና አማቼ ለማምለጥ ሲሞክሩ ከጀርባቸው ተመትተው ወደቁ። እኔ የተመታሁት ግራ ትከሻዬ ላይ ነበር። ተመትተው ከወደቁት ሰዎች መሃል ወደቅሁኩ፡፡ እንደሞትኩ አስመስዬ ዝም አልኩ፡፡ ስቃዬ ከባድ ነበር፤  ግን ዝም አልኩ፡፡ በኋላም በህይወት ለመትረፍ ዕድል አገኘሁ ሲል ምስክርነቱን ለተቋሙ ሰጥቷል፡፡
አምኒስቲ ከነዋሪዎቹ አገኘሁት ያለውን የምስክርነት ቃል ጠቅሶ እንደገለፀው፤ “የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ 12 የቀን ሰራተኞች እጃቸውን ወደ ኋላ የፊጥኝ ታስረው ጭንቅላታቸውን፣ደረታቸውንና ጀርባቸውን በጥይት ተመትተው ተገድለዋል፡፡
 ለአምኒስቲ ምስክርነቱን የሰጠው ግለሰብ ሲናገር “አስክሬኖቹን ያየሁት ከትምህርት ቤት አጥር አቅራቢያ ነበር፡፡ 20 አስክሬኖች በውስጥ ልብስ ብቻ ነበሩ፡፡ አብዛኛዎቹ የተመቱት ጭንቅላታቸው ላይ ነው፡፡ ከጀርባቸውና ከደረታቸው ላይም የተመቱ አሉ፡፡ ከጀርባ በኩል ጭንቅላታቸውን የተመቱት ሰዎች በጥይት የፊታቸው አካል በመበታተኑ ምክንያት ማንነታቸውን ለመለየት አይቻልም ነበር” ብሏል፡፡
የሰብአዊ መብት ተቋሙ 27 የዓይን ምስክሮችንና ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎችን በማነጋገርና መረጃዎችን በማሰባሰብ እና ከሳተላይት የተገኙ ምስሎች በመጥቀስ ባወጣው በዚሁ ሪፖርት፤ በርካታ ሰዎች በቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያናት መቀበራቸውን ማረጋገጡን ጠቁሞ፤ ይህም ነዋሪዎቹና የጥቃቱ ሰለባዎች ከሰጡት የምስክርነት ቃል ጋር የሚመሳከር ነው ብሏል፡፡
የአመነስቲ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ታጣቂ ቡድኑ ከሐምሌ ወር 2013  ጀምሮ በጭና ከተማና አካባቢው ላይ በፈጸመው ፆታዊ ጥቃት፣ ዕድሜያቸው 14 ዓመት የሚሆኑ በርካታ ሴት ታዳጊዎችንና እናቶችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈፅሞባቸዋል፡፡ ድርጅቱ አነጋገርኳቸው ያላቸው 14 የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ታዳጊዎች፣ በታጣቂ ሃይሉ በቡድን ወላጆቻቸው ፊት ተደፍረዋል፡፡ ለተቋሙ የምስክርነት ቃሏን የሰጠችው አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ፣ እሷና እናቷ በቡድን መደፈራቸውን ተናግራለች፡፡
ጊዜው ከረፋዱ 5 ሰዓት ግድም ይሆናል። መሳሪያ የታጠቁ ሁለት ወጣቶች ወደ ቤታችን መጡ፡፡ በወቅቱ እኔ እናቴና አያቴ ድርባህር አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታችን ውስጥ ተቀምጠን ነበር፡፡ ወደ ቤታችን ከዘለቁት ወጣቶች አንደኛው የወታደር ልብስ ለብሷል፤ አንደኛው ግን የለበሰው የአዘቦት ልብስ ነው፡፡ እርስ በርሳቸው እየተነጋገሩ ወደ ውስጥ ዘለቁ፡፡ የሚያወሩት ትግርኛና አማርኛ እየቀላቀሉ ነው “የኛ ቤተሰቦች ተደፍረዋል” አሁን ደግሞ “የእኛ ተራ ነው፣ የመጣነው ልንደፍራችሁ ነው” አሉን፡፡ አንደኛው እኔን እየጎተተ ይዞኝ ከቤት ወጣና በራፍ ላይ ደፈረኝ፡፡ ሌላኛው ደግሞ እናቴን እዛው  እናቷ ፊት ደፈራት፡፡ እናቴ አሁን በጣም ታማብኛለች፤ በወቅቱ ምን ተፈጥሮ እንደነበር እንኳን ማስታወስና ማውራት ፈፅሞ አንፈልግም” ብላለች-ታዳጊዎ፡፡
በዚሁ በጭና  ከተማ ውስጥ ከተደፈሩ ሴቶች መካከል  የ29 ዓመቷ ሠላም አንዷ ናት፡፡ ሠላም አራት የህወኃት ታጣቂ ሃይሎች እየተፈራረቁ ለ15 ሰዓታት ያህል አስገድደው እንደደፈሯት ለአምነስቲ ተናግራለች፡፡  ጥቃቱ ከተፈፀመባት በኋላ ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስባትም ህክምና ለማግኘት ባለመቻሏ  ህይወቷ አደጋ ላይ መውደቁንም ገልፃለች በሰጠችው ቃል፡፡
ታጣቂ ቡድኑ በቆቦ፣ጭናና ዙሪያው አካባቢዎች ካደረሰው የግድያና የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ባሻገር የጤና ተቋማትን ጨምሮ የግልና የመንግስት ንብረት የሆኑ በርካታ ተቋማትንም መዝረፉንና ማውደሙን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
አመኒስቲ ኢንተርናሽናል በሪፖርቱ ማጠቃለያ እንደገለጸው፤ ታጣቂ ቡድኑ የፈፀመው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ፣የጀምላ  ጭፍጨፋ የአስገድዶ መድፈር ወንጅል፣ ከጦር ወንጀል ጋር ሊስተካከል የሚችልና በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጅል ነው ብሏል፡፡  
ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፉ የሠብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ከሁለት ወራት በፊት ባወጣው የምርመራ ሪፖርት፤ በቆቦና በጭና አካባቢዎች በአጠቃላይ በትንሹ 97 ሰላማዊ ሰዎች በህወኃት ታጣቂዎች መገደላቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጫለሁ ሲል በሪፖርቱ


Read 9613 times Last modified on Sunday, 20 February 2022 15:24