ጀንቦሮ ሪል እስቴት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያጠናቀቃቸውን ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ለነዋሪዎቹ እደሚያስረክብ አስታወቀ።
ሪል እስቴቱ በዘርፉ የመኖሪያ አፓርመንቶችንና የንግድ ሱቆችን በማልማት ስራ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን በግሉ ዘርፍ መንግስት ያስቀመጠውን የመኖሪያ ቤት ችግር የመቅረፍ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የግሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ጀንቦሮ ሪል እስቴት በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የመኖሪያ አፓርትመንቶችንና የንግድ ሱቆችን እያለማ እንደሚገኝ አስታውሶ ከገነባውና እያስገነባ ከሚገኝባቸው ዘመናዊ የጋራ መኖሪያ ህንጻ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውንና በቦሌ ክፍለ ከተማ (ቦሌ ቡልቡላ) ወረዳ 12 የሚገኘውን 63 አባዋራዎችን ሊያኖር የሚችል ዘመናዊ አፓርትመንት አጠናቅቆ ዛሬ ቁልፍ እንደሚያስረክብ የሪል እስቴቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ቢረዳ አስታውቀዋል።
በዚህ የቁልፍ ማስረከብ ስነ-ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃፊዎች የክፍለ ከተማውና የወረዳው ተወካዮች የቤት ባለቤቶች ጋዜጠኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙም ታውቋል።
Published in
ዜና