Print this page
Saturday, 26 February 2022 12:03

“የመንግስት አስፈጻሚዎች ጣልቃ ገብነት ካለ ሃላፊነቴን እለቃለሁ”

Written by 
Rate this item
(0 votes)


             አዲስ የተቋቋመውን አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ በኮሚሽነርነት እንዲመሩ የተመረጡ አባላት በፍጹም ገለልተኛነት ሥራቸውን ለማከናወን ቃል የገቡ ሲሆን ኮሚሽነሩ ፕ/ር መስፍን አርአያ፤ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ካለ ከሃላፊነታቸው እንደሚለቁ አስታውቀዋል፡፡  
በዚህ የኮሚሽኑ ተልዕኮና ተግባር ውስጥ የመንግስት አስፈጻሚ አካል ጣልቃ ገብነት እንደማይኖር አምናለሁ ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ነገር ግን ከተሰጠው ውጪ  መንግስት እጁን የሚያስገባ ከሆነ ያለማመንታት ከሃላፊነቴ እለቃሁ ብለዋል።
ኮሚሽኑ በቀጣይ የተሳካ ምክክር ለማካሄድ በተለይ ከመገናኛ ብዙኃን ጋር በቅርበት እንደሚሰራና  ምልዐተ ህዝቡን በሚገባ ያሳተፈ ምክክር እንዲካሄድ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በዚህ  የምክክር ሂደት ዋነኛ ተሳታፊና ባለቤቱ  ህዝቡ እንደሚሆንና የፖለቲካ ድርጅቶች የዚሁ ምክክር ሂደት አንድ አካል እንደሚሆኑ በኮሚሽኑ አባላት የትውውቅ ፕሮግራም ላይ ተጠቁሟል።
የዚህ ኮሚሽን ዋነኛ ተልዕኮ በሀገሪቱ አወዛጋቢና አጨቃጫቂ  የሆኑ ጉዳዮች ላይ ምክክሮች እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን ምክክሩ ሊካሄድባቸው የሚችሉ የትኩረት አቅጣጫዎችም ተጠቁመዋል። ለአብነትም የባንዲራ ጉዳይ፣ የታሪክ ጉዳይ፣ ህገ-መንግስት ተጠቃሽ ናቸው፡፡  

Read 11270 times
Administrator

Latest from Administrator