Saturday, 26 February 2022 15:21

ለውድ የአዲስ አድማስ አንባቢያን፡-

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ትክክል ነው፡፡ ጋዜጣው ባለፈው ሳምንትም ዛሬም በዕለቱ አልወጣም፡፡ በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ብቸኛው የመንግስት ማተሚያ ቤት የሆነውና በቅርቡ 80ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከበረው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በየጊዜው ማሽኖቹ እየተበላሹ ጋዜጣችን በዕለቱ እንዳይወጣ እያደረገ ነው፡፡ በዓሉን ባከበረ ወቅት ይህንኑ ችግሩን ቢያምንም፣ መፍትሄውን ግን ገና ያሰበበት አይመስልም፡፡ መንግስት ጋዜጣ ማተም የሚችሉ ማሽኖች በግል ባለሃብቶች ወደ አገር ውስጥ መግባት የሚችሉበትን አሰራር ቢፈቅድ እንዲሁም አቅም ያላቸው ጋዜጦች የራሳቸው ማተምያ ማሽን ቢኖራቸው፣ መፍትሄ ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡ እስከዚያው ግን ከማተሚያ ቤቱ ጋር እየተነጋገርን በዕለቱ እንዲወጣ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ በነገራችን ላይ የመንግስት የህትመት ውጤቶች የሆኑት እነ አዲስ ዘመን ግን በዕለታቸው ነው የሚወጡት፡፡ የችግሩ ሰለባ የሆነው የግል ፕሬሱ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም በእኩል ዓይን የሚታዩበት ዘመን ይመጣል ብለን እናምናለን፡፡ በተቻለን መጠን የዲጂታል ሚዲያችንንም እያጠናከርን እንሰራለን፡፡ ጊዜው በፈቀደው ፕላትፎርም (ድረገጽ፣ፌስቡክ፣ዩቲዩብ፣ቴሌግራም ወዘተ) ሁሉ ለውድ አንባቢያን መረጃና ዕውቀት ማድረሳችንን እንቀጥላለን፡፡ በድጋሚ ለውድ አንባቢያን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ሳምንት በዕለቱ እንደምንወጣ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

Read 11438 times