Saturday, 05 March 2022 12:08

(HPV) --- አይነቱ ከመቶ በላይ ነው፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  (HPV) Human papillomavirus በቆዳ ንክኪ የሚተላለፍ የቫይረስ አይነት ነው፡፡
ወደ 40 የሚሆኑት (HPV) Human papillomavirus ለካንሰር ሕመም ይዳርጋሉ፡፡
ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) የተባለው ቫይረስ በአይነቱ ብዙ የተባለ ምናልባትም ከአንድ መቶ በላይ የሚሆን ነው፡፡ ይህ ቫይረስ ኢንፌክሽን ወይንም መመረዝን የሚያመጣ ሲሆን ይህ ጉዳትም ከሰው ወደሰው ቆዳ ለቆዳ በሚደረግ ንክኪ የሚተላለፍ ነው፡፡ መቶ ከሚደርሱት የቫይ ረሱ አይነቶች ውስጥ ወደ አርባ የሚሆኑት (HPV) በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ ከሰው ወደሰው የሚተ ላለፉ ሲሆኑ በዚህም የወንዶችን እና የሴቶችን ብልቶች እንዲሁም አፍን፤ የአየር ማስ ተላለፊያ  እና የምግብ መዋጫ ጉሮሮን የሚያጠቁ ናቸው፡፡ በዚህ እትም ምንጭ ያደረግነው February 15, 2021 በAlana Biggers, M.D., MPH (HPV) Human papillomavirus የተባለውን ቫይረስ በሚመለከት ለንባብ ያበቁትን ወደ አማርኛ መልሰነዋል፡፡
ወንዶች ወይንም ሴቶች በወሲብ ግንኙነት ምክንያት ከተጠቀሱት (HPV) አይነቶች ሊያዙ የሚችሉበት አጋጣሚ የሚኖር ሲሆን ምናልባትም ከብዙ ወይም ከተለያዩ ሰዎች ጋር የወሲብ ግንኙነት ማድረግ ብቻ መስፈርት ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም። ከአንድ ሰው ጋር ግንኙነት ቢያደ ርጉም ቫይረሱ አያጠቃም ማለት አይቻልም፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ በቫይረሱ ምክንያት በብ ልት አካባቢ የሚፈጠር ሕመም ወይም ሽፍታና ቁስለት ወደሌላ የጤና ችግር ላያመራ ይችላል፡፡ አንዳንድ (HPV) አይነቶች ግን እድገታቸው በብልት አካባቢ ቁስለትን የሚያደርሱ ሲሆን ከዚያም ባለፈ የማህጸን በር፤ ፊንጢጣ፤ ወይም የጉሮሮ ካንሰር ሊያመጡ እንደሚችሉ መዘንጋት አይገባም፡፡
ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) ያላቸው ብዙ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን እንኩዋን ሳያውቁ የሚቆዩበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ስለሆነም ምንም አይነት ሕክምና ሳይደርጉ ቫይረሱን ለሌላ ሰው ያስተላልፋሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እናቶች ልጅ በሚወልዱበት ጊዜ ቫይረሱን ለሚወለደው ልጅ ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ ህጻኑ በሚወለድበት ሰአት ይህ ቫይረስ ከእናቱ ሲተላለፍበት በምግብ ማውረጃ ጉሮሮአቸው ወይንም አየር ማስተላለፊያቸው ላይ ሊታይ ይችላል፡፡
የአሜሪካው በሽታ መቆጣጠርያና መከላከያ CDC  እንዳወጣው መረጃ ከሆነ ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) ሰዎችን ከያዘ ሁለት አመት በሚሆን ጊዜ ውስጥ በራሱ ጊዜ ሊጠፋ ይችላል፡፡ መረሳት የሌለበት ግን በዚህ ጊዜ ውስጥ ቫይረሱ የያዘው ሰው ወደሌላ ማስተላለፉን መቀጠሉ ነው፡፡ በተጠቀሰው መሰረት ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የማይጠፋ ከሆነ እና በየጊዜው እራሱን እያሳደገ የሚመጣ ከሆነ ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር እስከ ካንሰር ደረጃ ያስከትላል፡፡ በ(HPV) ምክንያት ከሚከሰቱ ሕመሞች መካከል የማህጸን በር ካንሰር አንዱና ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ የጤና ችግር ሲሆን ህመሙ ምንም ሳይታወቅ በመዝለቁ ምክንያት እናቶችን ለሞት ከሚዳርጉ እና በከፍተኛ ደረጃ ከሚጠቀሱ መካከል  ተጠቃሽ ነው፡፡
(HPV) ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ በወንዶች ላይ፡- ወንዶች በሂዩማን ፓፒሎማቫይረስ ሲያዙ ምንም ምልክት የላቸውም፡፡ ምንም እንኩዋን አንዳንዶች በብልታቸው እንደሽፍታ ወይንም ቁስለት የመሳሰሉ ነገሮች ቢታዩባቸውም የካንሰር ሕመም ለመሆኑ ምንም ማሳያ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ላይ ማለትም በፊንጢጣ፤ በብልት በመሳሰሉት ላይ ከተለመደው ውጭ የሆነ ምልክት ካየ በፍጥነት ወደ ሐኪም መሄድና ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡  
አንዳንድ የሂዩማን ፓፒሎማቫይረስ አይነቶች በወንድ ብልት፤ፊንጢጣ እና ጉሮሮ ላይ የካንሰር ሕመም ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ወንዶች እርስ በእርስ በሚያደርጉት ግንኙነት በቫይ ረሱ ምክንያት በፊንጢጣ ላይ ለሚከሰት የካንሰር ሕመም መጋለጣቸው በተደጋጋሚ ይስተ ዋላል፡፡ በተለይም በመዝናናት ስም ወይም ለተለያዩ ባእድ ሱሶች ከመጋለጥ አንጻር በሚፈጠር ልቅ የሆነ ወይንም ደህንነቱ ያልተጠበቀ የግብረስጋ ግንኙነት ሳቢያ ለአደጋ የመጋለጥ ሁኔታ የሰፋ ነው፡፡ በእርግጥ በብልት ላይ የሚታዩ ሽፍታዎች ወይንም እብጠቶች ሁሉ የካንሰር ምልክቶች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ የሌሎች ሕመሞች ምልክት መሆን ይችላል፡፡
(HPV) ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ በሴቶች ላይ፡- በተለያዩ ጥናቶች እንደተዘገበው 80 % የሚሆኑ ሴቶች በሕይወት ዘመናቸው አንዱ አይነት ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ሊይዛቸው ይችላል፡፡ ልክ እንደወንዶች ብዙ ሴቶች በሂዩማን ፓፒሎ ማቫይረስ ሲያዙ ምንም ምልክት አይኖራቸውም፡፡ በቫይረሱ ምክንያት የሚከሰተው ኢንፌክሽን ምንም ህመም ሳይሰማቸው ወይንም ሌላ ህመም ሳያስከትልባቸው ሊቆይ ወይንም ሊድን ይችላል፡፡
አንዳንድ ሴቶች በብልታቸው በተለይም በውስጠኛው ክፍል፤ በፊንጢጣቸው ወይንም በማህጸን በር የሚፈጠረው ቁስለት ወይንም እንደ ኪንታሮት የመሳሰሉ ሽፍታዎች መኖራቸውን ሲያውቁ በቀጥታ ወደ ሕክምና መሄድ ይኖርባቸዋል። ከዚህም ውጭ ያልለመዱት ነገር በሰውነታቸው ላይ ሲያስተውሉ በምንም ምክንያት ችላ ማለት የለባቸውም፡፡  ባጠቃላይም በብልት አካባቢ የሚከሰቱ ሕመሞች ጊዜ የማይሰጣቸውና አያዩ እንዳላዩ በመሆን የሚታለፉ አለመሆናቸውን ልብ ማለት ይገባል፡፡
HPV ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ መኖር አለመኖሩን ለማወቅ የሚደረገው ምርመራ በወንዶች እና በሴቶች ላይ ይለያያል፡፡ ሴቶች እድሜአቸው ለግብረስጋ ግንኙነት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ማለትም ከ20-21 ባለው እድሜ የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ (Pap smear) ማድረግ አለባቸው፡፡ እንዲያውም ከወንድ ጋር ምንም አይነት የግብረስጋ ግንኙነት ከመፈጸማቸው በፊት ክትባቱን ቢወስዱ ይበልጥ ይመከራል፡፡
ሴቶች እድሜአቸው ከ21-29 አመት ሲደርስ በየሶስት  አመቱ የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
እድሜአቸው ከ30-65 አመት ድረስ ያሉ ሴቶች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለባቸው፡፡
የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ በየሶስት አመቱ ማድረግ፤
የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ በተለይም ከፍተኛ ለሆነ ሕመም የሚዳርጉትን በሚመለከት በየአ ምስት አመቱ ምርመራ ማድረግ፤
የማህጸን በር ካንሰርን እና የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ምርመራዎችን co-testing በየአምስት አመቱ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል፡፡
በትንሹ አስራ አራት የሚሆኑት የፓፒሎማ ቫይረስ አይነቶች ወደ ካንሰር ሕመም ሊያመሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ ስለዚህም በሕክምናው መመሪያ መሰረት ክትትል ማድረግና የማህጸን በር ምርመራን በየጊዜው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
HPV ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ እንዴት ይይዛል?
ማንኛውም ሰው የግብረስጋ ግንኙነት በሚያደርግበት ጊዜ ቆዳ ለቆዳ ንክኪ ካለው በቫይረሱ ለመያዝ የተጋለጠ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለቫይረሱ የሚያጋልጡ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው ሲል መረጃው ያመለክታል፡፡
ከአንድ በላይ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ወሲብ መፈጸም፤
ጥንቃቄ በጎደለው መልኩ በብልት፤በአፍ ወይንም በፊንጢጣ ወሲብን መፈጸም፤
ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ካለበት ሰው ጋር ወሲብ መፈጸም፤
ህመምን ለመከላከል የማያስችል ደካማ የሰውነት የመቋቋም ኃይል፤
ህመሙ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ በሚያደርገው ሂዩማን ፓፒሎማ የቫይረስ አይነት እንዲያዙ የሚያደርጉ አንዳንድ ተያያዥ ምክንያቶች ኢንፌክሽኑ ወደ ካንሰርነት እንዲለወጥ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡
በሽታን ለመከላከል የማያስችል ደካማ የሰውነት የመቋቋም ኃይል፤
በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ እንደ ጎኖሪያ፤ቂጥኝ የመሳሰሉ ሕመሞች አስቀድሞውኑ ካሉ፤
ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ እብጠት ወይም ቁስለት፤
ብዙ ልጅ የወለዱ ከሆነ (የማህጸን በር ካንሰር)
ሲጋራ ማጥስ፤ሱስ አስያዥ እጾችን መውሰድ(የአፍ ወይንም የጉሮሮ ካንሰር)
በፊንጢጣ በኩል ወሲብ መፈጸም(የፊንጢጣ ካንሰር)
መረጃው እንደጠቆመው ከሆነ ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ቀላል መከላከያ አለው፡፡ እሱም በወ ሲብ ግንኙነት ወቅት ኮንዶም መጠቀምና ጤናማ ወሲባዊ ግንኙነት መፈጸም ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ Gardasil 9 vaccine የተባለ ክትባት በብልት አካባቢ የሚደርሱ ሽፍታ ወይንም ኪንታሮት መሰል ህመሞች ለመከላከልና ዘጠኝ አይነት ለካንሰር ሕመም የሚዳርጉ HPV ሂዩ ማን ፓፒሎማ ቫይረሶቸን ለመከላከል ይረዳል Alana Biggers, M.D., MPH እንዳስነበቡት፡፡


Read 11709 times