Saturday, 12 March 2022 14:23

‹‹ከባዶ ላይ መዝገን›› እና ‹‹የካህሊል አማልክት›› ለገበያ ቀርበዋል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በአምደኝነት የሚጽፈው ደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ ‹‹ከባዶ ላይ መዝገን›› እና ‹‹የካህሊል አማልክት›› የተሰኙ ኹለት አዳዲስ መጻሕፍትን ለገበያ አቅርቧል፡፡ የመጀመሪያው መጽሐፍ ‹‹ከባዶ ላይ መዝገን›› - (የዘመን ስካር ቅንጣቶች) ሲሆን ልዩ ልዩ ፍልስፍናዎች፣ ሒሳዊ ንባቦችና  ተምሰልስሎቶችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡ በ146 ገጾች ተቀንብቦ፤ በ200 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ሁለተኛው ‹‹የካህሊል አማልከት›› የተባለ ትርጉም ሲሆን፤ ‹‹Beloved Prophet›› ከተሰኘ የእውቁ ሊባኖሳዊ ገጣሚ፣ ሰዓሊና ደራሲ ካህሊል ጅብራንና የሜሪ ኤልዛቤት ሐስከል የሠላሳ ዓመታት የፍቅር ደብዳቤዎች ውስጥ ከፊሉን ያቀፈ የመጀመሪያ ቅጽ መጽሐፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡ መጽሐፉ በ145 ገጾች ተቀንብቦ፣ በ199 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡  ደራሲው በ2008 ዓ.ም ‹‹ሠለስቱ ጣዖታት›› የተሰኘ የልቦለድ መጽሐፍ ማሳተሙ አይዘነጋም፡፡

Read 3051 times