Print this page
Saturday, 12 March 2022 14:24

“ጥቂቶቹ” መፅሐፍ እየተነበበ ነው

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ባለፉት 20 ዓመታት ኑሮውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገውና 28 መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃው ደራሲ አለማየሁ ማሞ “ጥቂቶቹ” ሲል የሰየመው መፅሐፍ እየተነበበ ነው።
መፅሐፉ በዋናነት የኢትዮጵያ ባህር ሀይል አባላት አስደናቂ ግለ-ታሪኮች ላይ ያተኮረ ሲሆን “ጥቂት ግን ውጤታማ” (little but Effective) ብለው በአንድ ወቅት ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙሃን ያወደሱትና እንደወጣ የቀረው የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ታሪክ እንደቀልድ እንዳይዘነጋ ለማድረግ መፅሐፉ መሳናዳቱን ደራሲው ጠቁሟል።
ይህን መፅሐፍ ለማሰናዳት ሁለት ዓመታት እንደፈጀበት የገለጸው ደራሲው ከ1975-1982 ዓ.ም አገሩን ለሰባት ዓመታት በባህረኝት ማገልገሉንም ገልጿል። ይህ የባህር ሀይል አባላትን አስደናቂ ስራዎች ሰንዶ የያዘው “ጥቂቶቹ” መፅሐፍ በ288 ገጾች ተቀንብቦ በ250 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ከሽያጩ ገቢ የሀገር ውለታ ሲውሉ ለደከሙ፣ ለታመሙና ደጋፊ ላጡ አንጋፋ የባህር ሀይል አባላት መደጎሚያ እንደሚውልም ደራሲው ገልጿል። መጽሐፉ በጃዕፈርና በሮማናት መጻህፍት  መደብሮች በዋናነት እተከፋፈለ ሲሆን በሁሉም መጽሐፍ አዟሪዎች እጅ እንደሚገኝም ታውቋል።

Read 11230 times