Saturday, 12 March 2022 14:26

“የሚያደንቁትን ሰው ያግኙ ይተዋወቁ “አዲስ ሁነት ሊጀመር ነው

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   “ታዋቂ ኢቨንትስ” ሰዎች የሚያደንቋቸውንና የሚወዷቸውን ሰዎች የሚያገኙበት፣ የሚተዋወቁበትና ጥሩ ጊዜ የሚያሳልፉበትን እድል የሚፈጥር አዲስ ሁነት ማዘጋጀቱን አስታወቀ “የሚያደንቁትን ያግኙ ይተዋወቁ” (Ethiopian Celebrate Meet And Greet) የሚል መጠሪያ ያለው ይሄው ሁነት መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ  ሆቴል ታዋቂዋን የፊልም ተዋናይት ሰላም ተስፋዬን ከአድናቂዎቿ ጋር  በማገናኘት ሥራውን እንደሚጀምር የታዋቂ ኢቨንተስ ሀላፊዎች ትላንት የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
መርሃ ግብሩ ዝነኞችን ለሚያከብሯቸውና ለሚያደንቋቸው  ሰዎች ለማገናኘት በወር አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ መሆኑም ታውቋል፡፡ ተሳታፊዎቹ የእራት ግበዣ፣ ከሚያደንቁት ወይም ከሚያደንቋት ዝነኛ ጋር ፎቶ የመነሳት፣ ሥጦታ የመለዋወጥ፣ የመተዋወቅና የምስጋና ሥነ-ስርዓቶች የሚያከናውኑበት ነውም፣  ተብሏል፡፡
ይህ ሁነት ለዝነኞቹም ሆነ ለአድናቂዎች የሚያስገኘው ጥቅም አለው ያሉት የተዋቂ ኤቨንትስ ሀላፊዎች፣ዝነኞቹ እውነተኛ አድናቂዎችንና አክባሪዎቻቸውን የሚያገኙበት ሲሆን አድናቂዎች የሚያደንቁትንና ሊያገኙት የሚመኙትን ዝነኛ ሰው በአካል በማግኘት ስሜታቸውን አድናቆታቸውንና ክብራቸውን ለመግለፅ እድል ከማግኘታቸውም በላይ ፊርማ የማስፈረም፣ የማስታወሻ ፎቶ የመነሳትና የመወያየት እድል ይፈጥርላችዋል ብለዋል፡፡

Read 11268 times