Saturday, 12 March 2022 15:30

መልዕክቶቻችሁ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በባንኮች የተፈጠረው መተረማመስ የማን ጥፋት ነው?!

            ብሔራዊ ባንክ ሁሉም ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ እንዲያሟሉ በቅርቡ ያወጣው መመርያ ቀነ ገደቡ በመተላለፉ ባንኮች ሌላ አገልግሎት መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ እየተተራመሱ ነው። ሕዝቡም እንደፈረደበት የገዛ ገንዘቡ ታግቶበት፣ በጠራራ ጸሃይ ሰልፍ ተራ ገብቶ  እየተተራመሰ ነው። ለማን አቤት ይባላል?!
ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የተከማቹና በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደንበኞችን መረጃ የማሰባሰብ ውዝፍ ስራ በወራት እንደማይገባደድ እየታወቀ፣ ቀኑን ከማራዘም ይልቅ የሕዝቡን ገንዘብ አግቶ ማተራመስ፣ ሕዝብ እንደለመደው ይሰለፋል እንጂ ምን ያመጣል የሚል ንቀት ይመስላል።
የሀገራችን ተቋማት ስራቸውን በእቅድና በአግባቡ ከመስራት ይልቅ ስራን ለዘመናት ወዝፈው እየኖሩ በድንገት ከእንቅልፉቸው ሲነቁ፣ ሕዝብ ላይ ሱሪ ባንገት ቀጭን ትዕዛዝ እየጫኑ ማተራመሳቸውን የሚያቆሙት መቼ ነው?
በንዝህላልነታቸውስ ምክንያት ሕዝቡ ለሚደርስበት መጉላላት ተጠያቂነታቸው የት ድረስ ነው? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ለስንቱ ተቋም አምባገነንነት ጎበስ ቀና እያለ ይኑር?
(ሙሼ ሰሙ)



Read 1563 times