Saturday, 19 March 2022 10:39

የኢቢሲ የኦሮምኛ ክፍል ኃላፊ በግማሽ ሚሊዮን ብር ጉቦ በመቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰሰ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ከርፖሬሽን (EBC) የኦሮምኛ ክፍል ኃላፊ በላቸው ጃቤሳ፣ ከሸገር ውሀ አምራች ድርጅት ሀላፊ ግማሽ ሚሊዮን ብር ጉቦ በመቀበል በከባድ ሙስና ወንጀል ተከሰሰ። ከበላቸው ጀቤሳ ጋር የሰበታ ከተማ ወረዳ 08 ነዋሪ የሆነው  አለማየው ቂጢባ የተባለ ግለሰብም የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።
1ኛ ተከሳሽ በላቸው ጀቤሳ የEBC ኦሮምኛ ክፍል ሀላፊ ሆኖ ሲሰራ፣ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር በመመሳጠር  የሸገር ውሀ አምራች ኩኒስ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላፊነት የተወሰነ ማህበር ድርጅት  የሚያመርተውን የውሀ ምርት ባዓድ ነገር እንዳለው በሚዲያ እንደሚቀርብ ማስፈራራታቸው በክሱ ተመላክቷል።
 በዚህም 2ኛ ተከሳሽ በጥር ወር 2014 ዓ/የድርጅቱ ባለሀብት ወደሆነው ዶ/ር ሀሰን መሀመድ ሩር ስልክ በመደወል አዳማ ከተማ አንድ ሱቅ ውስጥ ውሀ ለመጠቀም ገዝቼ ሶፍት መሳይ ቆሻሻ ስላገኘሁበት በጥር 26 እና 27 ቀን ለኢትዮጲያ ብርድካስት ኮርፖሬሽን ጥቆማ ያቀረብኩ በመሆኑ    
በላቸው ጃቤሳ የተባለ የEBC ሰራተኛ አናግሩ በማለት የ1ኛ ተከሳሽን ስልክ ለውሀ አምራች ድርጅት ባለቤት ለዶ/ር  ሀሰን መሀመድ መስጠቱ  በክሱ ተገልጿል።
 ባለሀብቱም በተሰጣቸው ስልክ ለ1ኛ ተከሳሽ ለEBC ኦረምኛ ክፍል ሀላፊ ለበላቸው ጀቤሳ ስልክ በመደወል በአ/አ ብሔራዊ አካባቢ በሚገኝ ራስ ሆቴል በመገናኘት ይኺው 1 ተከሳሽ የውሀው ጥቆማ ለተቋሙ የደረሰ መሆኑን ገልጾ ነገር ግን በሚዳያው እንዴይተላለፍ  ከፈለጉ ገንዘብ እንዲከፍሉ መጠየቁ ተመላክቷል በክሱ።
 በጥር 28 ቀን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ /ከ ለቡ ጋርመንት አካባቢ በሚገኝ አንድ ካፍቴሪያ  ከባለሀብቱ ጋር በመገናኘት ወደ ለተቋሙ የደረሰው በምስል የተደገፈ ጥቆማ  እንዲመለስ ከፈለጋችሁ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ከጠየቁ በኋላ ባለሀብቱ በገንዘቡ መጠን ሳይስማሙ ከተለያዩ በኋላ በድጋሚ በየካቲት 2 ቀን 2014ዓ/ም ደግሞ በዛው ቦታ ተገናኝተው ባለሀብቱ ዶ/ር ሀሰን መሀመድ  100 ሺህ ብር በጥሬው ለ1ኛ ተከሳሽ ሰተውት ተከሳሹም ብሩን መኪና ውስጥ ካስገባ በኋላ ቀሪውን የ400 ሺህ ብር ሶስት ቼክ ደግሞ መኪና ውስጥ ሲቀበሉ በፌደራል ፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ መያዛቸው በክሱ ተዘርዝሮ  ጉቦ በመቀበል ከባድ ሙስና ወንጀል ክስ  ቀርቦባቸዋል። ተከሳሾቹ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጽ/ቤት ቀርበው የክስ ቻርጁ እንዲደርሳቸው ተደርጓል። ፍርድ ቤቱ ክሱን በችሎት በንባብ ለማሰማት  ለመጋቢት 12 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Read 8756 times