Saturday, 19 March 2022 10:52

የንጉሡ አንዳንድ ትሩፋቶች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

= በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን በመላው ኢትዮጵያ 9 ሆስፒታሎችና 113 ባንኮች ነበሩ።
= ከኢጣሊያ ወረራ በፊት በኢትዮጵያ 30 ትምህርት ቤቶችና 5ሺ ተማሪዎች ነበሩ። ከወረራው በኋላ ከ1933- 1966 ዓ.ም ድረስ 1999 ት/ቤቶች፣
17 ኮሌጆችና 2 ዩኒቨርሲቲዎች ተከፍተዋል።
= በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን 423 ልዩ ልዩ ፋብሪካዎች ተቋቁመው ነበር።
= በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን ኢትዮጵያ 16 የጦር መርከቦች፣ 2 ሰርጓጅ መርከቦች ነበሯት።
= በንጉሡ ጊዜ በአገሪቱ 573 ልዩ ልዩ ባቡሮችና ጋሪ የምድር ባቡሮች ነበሩ።
= ኢትዮጵያ ከ1921-1928 ዓ.ም 17 አውሮፕላኖች፤ ንጉሡ በድል ከተመለሱ በኋላ 238 ልዩ ልዩ የመንገደኞች፣ የጦር አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች የነበሯት ሲሆን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች 41 አውሮፕላን ማረፊያዎች ተሰርተው ነበር።
= ኢትዮጵያ በጠላት የተወሰዱባትን ወደቦቿንና ሌሎችም ግዛቶቿን ለማስመለስ የቻለችው በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ነበር።
= የመጀመሪያ የተጻፈ ሕገ-መንግስት በኢትዮጵያ የታወጀው በቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ነው።
= ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የዐፄ ቴዎድሮስን ዘውድና ልዩ ልዩ የክብር እቃዎች ከወራሪዎች አስመልሰዋል። ለገሃር (ባቡር ጣቢያ) የሚገኘውን የይሁዳ
አንበሳ ሃውልት ያስመለሱትም ንጉሡ ናቸው።
= ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከፖርቱጋል መንግስት ሐምሌ 23 ቀን 1951 ዓ.ም የአገሪቱን የመጨረሻውን የጄኔራልነት ማዕረግ፤ ከእንግሊዝ መንግስት ጥር
24 ቀን 1957 ዓ.ም የፊልድ ማርሻልነት ማዕረግ አግኝተዋል።
(ምንጭ፡- የግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ መታሰቢያ ማህበር መጽሔት)

Read 1196 times