Saturday, 02 April 2022 11:33

“የአማራ ለዛ” የኪነ ጥበብ ምሽት ትላንት በባህርዳር ተካሄደ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  “የአማራ ለዛ” የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት ትላንት መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ባህር ዳር በሚገኘው ሙሉዓለም የባህል አዳራሽ ተካሄደ፡፡ የአማራ ህዝብ ያለውን ሰፊ ባህል፣ ትውፊት ኪነ ጥበብ እና አብሮነት መሰረት አድርጎ በተሰናዳው የኪነ ጥበብ ምሽት ላይ ግጥም፣አነቃቂ ንግግር፣ዲስኩር፣ሙዚቃና አጭር ቴአትር በታዋቂና አዋቂ ምሁራን ከያንያን ለታዳሚ መቅረቡን በአማራ ክልል የሙሉአለም ባህልና ኪነ ጥበባት ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማሪያም ይርጋ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
በዕለቱ ከተዘረዘሩት ኪነ ጥበባዊ ሁነቶች በተጨማሪ ግንባታው ከተጀመረ 11ኛ ዓመቱን የያዘው ታላቁን የህዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨት ተከትሎ  የትውልዱን እድለኝነትና ተስፋ በማሰብ ህዝባዊ ተሳትፎው እንዲቀጥል የሚያነሳሱ ክንዋኔዎች እንደቀረቡም አቶ ገብረማሪያም ይርጋ ገልፀው የኪነ ጥበብ ምሽቱም ቀጣይነት እንደሚኖረውም ጠቁመዋል፡፡

Read 41074 times